የድሬዳዋ ከተማን የቀደመ ሠላም ለመመለስ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ተባለ

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8B%A8%E1%8B%B5%E1%88%AC%E1%8B%B3%E1%8B%8B-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B0%E1%88%98-%E1%88%A0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%88%88%E1%88%98%E1%88%98%E1%88%88%E1%88%B5/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማን የቀደመ ሠላም ለመመለስ ሁሉም አካላት ርብርብ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያዘጋጀውና በድሬዳዋ ሠላምና ፀጥታ ዙሪያ ያተኮረ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ከሪማ አሊ፥ ድሬዳዋ ከዚህ በፊት የምትታወቅበት የሠላምና አብሮ የመኖር እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር እንዳወቅ ፀጋ፥ ሠላም የሁሉም ነገር መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

ለአሁናዊ የድሬዳዋ የሠላም መደፍረስ የስራ አጥነት መስፋፋት፣ የፖለቲካ የስልጣን ሽኩቻ፣ መደበኛ ያልሆኑ አደረጃጀቶች መበራከትና የወጣቱ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።

አያይዘውም የድሬዳዋን የቀደመ ሠላም ለመመለስ የቋንቋና የባህል ልዩነትን በማክበር፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ ፅንፈኛና ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦችን ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ረዳት ኢንስፔክተር ባንታለም ግርማ፥ ፖሊስ የአካባቢ ፀጥታን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የድሬዳዋ የቀደመ ሠላም እንዲመለስ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አደጃጀቶችን በማጠናከር ድርሻውን እንደሚወጣ ጠቅሰዋል።

ህብረተሰቡም ትናንሽ ግጭቶች እንዳይስፋፉ ማድረግና ቤተሰቦችም ልጆቻቸውን መምከር እንደሚኖርባቸውም አውስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ በአግባቡ አለመመለሱ፣ የወጣቶች የስብዕና ማዕከላት በአግባቡ አለመስፋፋት እንዲሁም የፖለቲካ አደረጃጀቱና የስልጣን ሽኩቻ ለሰላም እጦት ምክንያት መሆኑን አንስተዋል።

የአስተዳደሩ አመራሮችም ከህዝቡ ጋር በመነጋገር የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የድሬዳዋ የቀደመ ሠላም እንዲመለስ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

 

በተሾመ ኃይሉ

 

Share this post

2 thoughts on “የድሬዳዋ ከተማን የቀደመ ሠላም ለመመለስ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ተባለ

  1. Removing ODP’s grip from Dire Dawa city administration is the only solution. Dire Dawa people deserve to administer themselves. Dire Dawa city is unfairly being governed by ODP in a city where majority of the residents are not Oromo. Demography change must not only stop but also must get reversed in Dire Dawa.

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.