የድጋፍ ሰልፎች

Source: https://amharic.voanews.com/a/pp-support-2-20-2020/5297175.html
https://gdb.voanews.com/BEE55E25-DFE8-40BD-98DE-179B7EA83857_cx0_cy22_cw0_w800_h450.jpg

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና ብልጽግና ፓርቲ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ በምስራቅ ሐረርጌ አንዳንድ ቦታዎች ላይ እክል እንዳጋጠመው የሰልፉ ተሳታፊዎች ገለፁ።

በሻሽመኔ ከተማ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል።

በሌላ በኩል በጋምቤላ ከተማ የብልፅግና ፓርቲንና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የለውጥ ሥራዎች የሚደግፍ ሰልፍ መካሄዱ ታወቀ።

“መነሻችን መደመር መድረሻችን ብልፅግና” የሚልና ሌሎችም መፈክሮች ሲያሰሙ እንደነበር ከሰልፈኞች መካከል ገልፀዋል።

የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት “ብልፅግና እውነተኛ የዲሞክራሲና ፌዴራላዊ ሥርዓትን የሚያረጋግጥ ነው” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.