የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ነገር – ( አቻምየለህ ታምሩ)

Source: http://welkait.com/?p=15657

የ«ያ ትውልድ» ግብታዊ የፖለቲካ ንቅሳቄ በርካታ አቋም የሌላቸውን ምሁራንና የፖለቲካ ተዋናዮች ፈጥሯል። ከነዚህ አቋምና integrity የሌላቸው የ ያ ትውልድ የፖለቲካ ንቅናቄ ካፈራቸው ሰዎች መካከል ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ቀዳሚው ናቸው። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በተለያየ ጊዜ የሚጣረሱ አቋሞችን የሚሰጡና የሚጋጩ ምስክርነቶችን የሚናገሩ ሰው ናቸው። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እ.ኤ.አ. በ2015 ዓ.ም. አሜሪካን አገር ከርመው ወደ አገር ቤት ከመመለሳቸው …

Share this post

One thought on “የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ነገር – ( አቻምየለህ ታምሩ)

 1. *** በቅድሚያ አማራ ጠል የጫካው ማኒፌስቶ ሻዕቢያ፡ የህወሓት፡ ኦነግ፡ ኦብነግ የተገንጣይ አስገንጣይ ቃል ኪዳን ሲሆን የከተማው ሕገመንግስት ሲሆን ‘በልዩ ጥቅማጥቅም’ ሁሉን የጠረነፈ ነው። ሕጻን ልጅ እየበላ ያልቀሳል ይሏል የእነዚህ ዓይነት አልቅቶች ለራሳቸውም ለኦሮሞም አልሆኑም ጨዋና የዋሁን ሀገር ወዳድ ኦሮሞ አፍዘው አደንዝዘው ፵፬ ዓመት አስበሉት፡የበይ ተመልካች አደረጉት፡አረመኔ ጭፍጫፊ ተገንጣይ አሸባሪ አሰኙት እንጂ ምን አተረፉለት? እነኝህ ቁጥር መሙሊያ እንጂ ለሀገር ይጠቅማሉ ማለት ግን ዘበት ነው፡፡

  ዛሬም የተበከለ የማተራመስ አባዜ ያላቸው እርዝራዦቻቸው ሰላም! አንድነት! ፍቅር ! ሲሰበክ አይወዱም። ጥቅማጥቅማቸው ይነካል (በከብት ጋጣ) ክልል ታጉረው የሚበሉበትና የሚያባሉበት የቋንቋና ነገድ ተኮር ፌደራሊዝም፡ “ቋንቋ ባሕልና ሃይማኖታችንን ትበርዛላችሁ ልዩ ነን አትድረሱብን የእናንተ ግን የእኛም ነው” የሚሉ ቡጥቦጣቸው ይስተጓጎልባቸዋል ለነገሩ ዓብይ አህመድም ደርሶባቸዋል በወያኔ ትግሬ አመካኝተው የሚያደናቃቅፉትን የውስጡ ደንቃራዎች ቀስ እያለ ይመነጥራቸዋል! ‘በታወቁና በተከበሩ’ ኒሻን አጋጣሚውን ፈልገው አትርሱን እያሉ በየሚዲያው ወሬ ጠሽ! ዕጧ! እያረጉ ሞታቸውን ከመጠበቅ ውጪ ለድምር አልተፍጠሩም ።
  +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
  መደ’መር ማለት…ለሀገረ ኢትዮጵያ ባለን ገንቢ ሐሳብ ላይ አዲስ ሓሳብ አፍልቀህ ጨምረበት” ማለት እንጂ ሰው ቆጠራ አደለም።አራት ነጥብ።
  ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
  ነጋሶ ገዳዳ በቅርቡ ሕገመንግስቱን አሻሽላለሁ እያለ ሲደነፋ አልነበረም ዛሬ ምን ተገኘ ?….ይህ ሰው የአንድነት ፓርቲ መሪ ሆኖ መተዳደሪያ ደንቡ የገባው ሲባረር አደለም!? ሰለባሌጎባ ታሪክ አጥንቶ ስለሐረር የታሪክ መጽሐፍ የሚሸቅል አደለም!? ለመሆኑ የኢህአዴግ ፕሬዘዳንቶች ሥራቸው ምንድነው?
  ************************
  አሁን በሥራ ላይ ያለው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ እንዴት ነበር በህገ መንግስቱ የተካተተው ?
  በመጀመሪያ በህገ መንግስቱ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች ብለን፣ ረቂቅ ሃሳቦችንና ጉዳዮችን ሰብስበን በዝርዝር አሰፈርን፡፡ በጥያቄ መልክ 73 ጉዳዮችን ነው በዝርዝር ያስቀመጥነው፡፡ እነዚህን 73 ጥያቄዎች ደግሞ ቅርፅ ያስያዙልን ኤክስፐርቶች (ባለሙያዎች) ነበሩ፡፡ ጥያቄዎቹ ተዘርዝረው የነበረው በመጠይቅ መልክ ሲሆን “ድጋፍ”፣ “ተቃውሞ” በሚል ተለይተው ነው፣ የህዝብ አስተያየት የተሰበሰበባቸው፡፡ የተቃውሞና ድጋፍ ውጤቱ የተሰላውም በመቶኛ ነበር፡፡
  እስቲ ለምሳሌ ያህል ይጥቀሱልን— ?
  ለምሳሌ አጨቃጫቂው የህገ መንግስቱ አንቀፅ 39 ማለትም፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠልን የሚፈቅደው በመጠይቅ ዝርዝሩ ተካትቶ ነበር፡፡ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ደግሞ በተመረጡ 23 ሺህ ቀበሌዎች ላይ ነው የህዝብ ውይይት የተደረገው፡፡ እኔ ለምሳሌ ደምቢዶሎ ላይ አወያይቻለሁ፡፡ ደምቢዶሎ ትልቅ ከተማ ነው። ህዝቡ ከ50 ሺህ አያንስም ግን እኔ ያወያየኋቸው ከ200 አይበልጡም፡፡ በዚህ አይነት ነው ውይይቶች የተካሄዱት፡፡
  በዚህ መሰረት ለምሳሌ አንቀፅ 39 (የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል) ላይ በክልል አንድ (ትግራይ) መቶ በመቶ ድጋፍ አግኝቷል። በክልል ሁለት (አፋር) ደግሞ ይህ አንቀፅ 98 በመቶ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ በክልል 3 (አማራ ክልል) 89 በመቶ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ክልል 4 (ኦሮሚያ ላይ) 97 በመቶ ድጋፍ አኝቷል፡፡ ክልል 5 (ሶማሌ) 72 በመቶ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ክልል 6 (ቤኒሻንጉል ጉሙዝ) 88 በመቶ ነበር ድጋፍ ያገኘው፡፡ ክልል 12 (ጋምቤላ) ደግሞ 59 በመቶ ድጋፍ አግኝቷል፡፡
  የሰንደቅ ዓላማው ጉዳይ እንዴት በህገ መንግስቱ ላይ ተደነገገ ታዲያ?
  አርቃቂ ኮሚሽኑ የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ መግባት አለበት ብሎ በራሱ አስገብቶት ነው፡፡ ኮሚሽኑ በእንዲህ መልኩ የሰንደቅ አላማውን ጉዳይ በአንቀፅ 3 አስቀምጦ፣ ከየክልሉ ለተውጣጡትና የህገ መንግስት ጉባኤ አባላት አቅርቦ ነበር፡፡ በዚህ አንቀፅ ስር ሶስት ንኡስ አንቀፆች አሉ፡፡ የአርማ ጉዳይን፣ የክልሎች ሰንደቅ አላማን የተመለከቱ ናቸው፡፡ በጉባኤው በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙም ክርክር አልተካሄደም ነበር፡፡ በጉዳዩ ላይ ውይይት የተደረገው፣ ለሁለት ቀናት ማለትም፣ ጥቅምት 29 እና 30፣ 1987 ዓ.ም የነበረ ሲሆን በሰንደቅ ዓላማው ጉዳይ ሃሳባቸውን የሰጡ ሰዎች 37 ብቻ ነበሩ፡፡ ሰንደቅ ዓላማውን በተመለከተ የቀረበውን ረቂቅ ድንጋጌ፣ 513 የጉባኤው አባላት ድጋፍ ሲሰጡበት፣ በ4 ተቃውሞና በ5 ድምፀ ተአቅቦ ነው ፀድቆ፣ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 3 በመሆን የተደነገገው፡፡
  በወቅቱ የአርማው መቀመጥ ጉዳይ ላይ የቀረበ ጠንካራ ተቃውሞ አልነበረም?
  ብዙም አልነበረም፡፡ አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ብቻ ነበር “የአርማና የባንዲራ ልዩነት ምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ ያቀረበው እንጂ ብዙም ጠንካራ ክርክርና ጥያቄ አልተነሳም፡፡ ሻለቃ አድማሴም እንዲሁ ተቃውሞ አቅርበው ነበር፡፡ ከክልል 5 (ሶማሌ) የተወከሉት አቶ አሊ አብዱ፤ ሶስቱ ቀለማትና አርማው እንዳለ ሆኖ፣ “ነጭ” ቀለም ይጨመርበት የሚል ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡ ከአፋርም እንዲሁ ነጭ ቀለም ይጨመርበት የሚል ሀሳብ ተሰንዝሮ ነበር፡፡ በዚህ የአርማ መጨመር ጉዳይ ላይ በተሰጠው የጉባኤው አባላት ድምፅ መሰረት፤ 517 ሰዎች አርማ መጨመር አለበት ሲሉ፣ 4 ተቃውሞ እንዲሁም 4 ድምፀ ተአቅቦ አድርገው ነበር፡፡
  የክልሎች ሰንደቅ አላማን በተመለከተስ — የተነሱ ሃሳቦችና ክርክሮች ነበሩ?
  አሁን በህገ መንግስቱ አንቀፅ 3 ንኡስ አንቀፅ 3 ስር ተደንግጎ የሚገኘውና “የፌደራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ አላማና አርማ ሊኖራቸው ይችላል” የሚለውን በተመለከተ፣ ብዙም የተቃወመ አልነበረም፡፡ ነገር ግን “ብቻውን የሚውለበለብ ሳይሆን ከፌደራሉ ጋር ጎን ለጎን ነው የሚውለው” በሚለው ላይ የተወሰኑ ሃሳቦች ተሰንዝረው ነበር፡፡ በዚህ ጎን ለጎን መውለብለብ አለባቸው በሚለው ጉዳይ ላይ በተሰጠ ድምፅ፡- ድጋፍ 5፣ ተቃውሞ (ጎን ለጎን መሰቀል አያስፈልግም ያሉ) ደግሞ 517 ነበሩ፡፡ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉ 8 ነበሩ፡፡
  አሁን ግን ከፌደራሉ ጎን ለጎን መሆን አለበት የሚል መመሪያ ወጥቷል ….
  ይሄ እንግዲህ በህገ መንግስቱ ያልተወሰነ፣ ነገር ግን በመመሪያ የወጣ ይመስለኛል፡፡
  በፌደራሉ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የቀረቡ ሌሎች ሃሳቦችስ ነበሩ?
  እንግዲህ ይሄ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማት በዓለም ላይ የታወቅንበት፣ የነፃነት አርማም ስለሆነ መቀየር አያስፈልግም፤ ነገር ግን በመሃሉ የሃይማኖት፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትን የሚወክል አርማ የግድ መኖር አለበት—የሚል ሃሳብ ነው በስፋት የተሰነዘረው፡፡
  በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሠንደቅ ዓላማ ጉዳይ ከፍተኛ አለመግባባትና ልዩነት እየተፈጠረ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው ብለው ይገምታሉ?ቀደም ብሎ እኔ እንደማውቀው፣ የኢህአዴግ ስብሰባዎች ካልሆኑ በስተቀር ብዙ ጊዜ ህዝቡ ይዞ የሚወጣው ሌጣውን ነበር፡፡ በተለይ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል አካባቢ በተለይ ኮከቡ ያለበትን ሠንደቅ ዓላማ ተቃውሞ እንደሚቀርብበት በሚገባ የተመለከትኩት፣ በእነዚህ ሁለት ዓመታት (2008 እና 2009) ጊዜ ውስጥ በተፈጠሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ላይ ነው፡፡ በተቃውሞዎቹ በግልፅ በባለኮከቡ ሠንደቅ ዓላማ ያለው ተቃውሞ በአብዛኛው ታይቷል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይሄን ሰንደቅ ዓላማ ይቃወማሉ፡፡
  አስቀድሜ እንዳልኩት፣ ይህ አሁን መመሪያ ወጥቶለት በግድ ሊተገበር በታሠበው ሠንደቅ ዓላማና አርማ ላይ ህዝቡ ውይይት አላደረገበትም። በሌላ በኩል ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች በእኩል በሂደቱ አልተሣተፉም፡፡ ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ኦነግ፣ ኢሠፓ ሌሎችም በዚህ ሂደት አልተሣተፉም። እነዚህ ኢትዮጵያውን ናቸው፣ ደጋፊዎች አሏቸው፤ ነገር ግን በሠንደቅ ዓላማው ጉዳይ ውይይት አላደረጉም፡፡ በህገ መንግስቱ ላይም እንዲሁ። በሌላ በኩል፤ በረቂቅ ህገ መንግስቱ ላይም ሆነ በፀደቀው ህገ መንግስት ላይ ህዝቡ የራሱ ፍላጎት ስለመካተቱ የሚያንፀባርቅበት ህዝበ ውሣኔ አልተካሄደም፡፡ እንዳለ ወደ ህዝቡ ነው ፀድቆ የወረደው፡፡ የሠንደቅ ዓላማው ሆነ ሌሎች ችግሮች የሚመነጩት፣ አንደኛው ከዚህ አንፃር ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ላይ ህዝበ ውሣኔ ካልተካሄደበት ስርአቱ ወይም ህገ መንግስቱ በህዝቡ ተቀባይነት እንዳለው ማረጋገጫ ማቅረብ አይቻለውም ማለት ነው፡፡
  አሁንም የሚሻለው በህገ መንግስቱም ሆነ በሠንደቅ አላማው ጉዳይ ላይ የማሻሻያ ሃሣቦች ካሉ፣ ማሻሻያ ይደረግ የሚሉ አካላት ፊርማ አሠባስበው ቢያቀርቡና፣ ጉባኤ ተደርጎ፣ ለህዝብ ውሳኔ ቢቀርብ ነው፡፡ ሁነኛ መፍትሄ የሚሆነው ህዝበ ውሣኔ ማካሄድ ነው፡፡(ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፡- በሰንደቅ ዓላማና በህገ መንግስቱ ዙሪያ በጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ) ኦክቶበር 14/2017

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.