የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ሚስጢር ሲገለጥ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/182152

(በነብዩ ስሑል ሚካኤል ተፃፈ)
የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ሚስጢር ሲገለጥ፤
ባለፈው ኣርብ በዋልታ ቴሌቪዥን የፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣው የደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶ ተከትሎ የመላ የኣገራችን ህዝብ ላይ ድንጋጤና ኣግራሞት መፍጠሩ ይታወሳል፡፡ እንደሚታወቀው የተሰራጨው መረጃ ወድያዉኑ ከዋልታ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንዲጠፋና በማረምያ መረጃ እንዲተካ የተደረገ ሲሆን ቀጥሎም የቴሌቪዥን ጣብያው የበላይ ሃላፊዎች በሰጡት ማብራርያ ጉዳዩ ከእውቅናቸው ውጭ እንደተፈፀመና ይህን የመሰለ የተቀነባበረ የፈጠራ ወሬ ሊነዛ የሚፈልግ የኣገራዊ ለውጡ ተቃዋሚ የሆነ ሃይል እንደሚሆን ፍንጭ ሰተዋል፡፡
የዶ/ር ደብረፅዮን የፈጠራ ሞት መርዶው ከተሰማበት ቅፅበት ጀምሮም ብዙ ሰው ስለጉዳዩ መረጃ ሲሰበስብ፣ ሃሳብ ሲያብላላና ትንበያዎች ሲለዋወጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ እኔም በበኩሌ የድርጊቱ ኣላማ ምን ሊሆን እንደሚችልና ፈፃሚዎቹ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃ ሳሰባስብና ከብዙ ሰዎች ጋር ሃሳብ ስለዋወጥ ቆይቻለሁ፡፡ ዋልታ ቴሌቪዥንም ስለ ድርጊቱ እወነተኛ መረጃ እስኪያቀርብልንና ህጋዊ እርምጃው እስኪያሳውቀን ድረስ እንሆ ኣንድ የድርጊቱ ፈፃሚ ኣካል ከፍተኛ ትንበያና ሁለት ድርጊቱ እንዲፈፀም ያስፈለገበት ኣሳማኝ ኣመክንያዊ-ኩነቶች/Reasonable-Scenarios፡-
የድርጊቱ ፈፃሚ ኣካል ከፍተኛ ትንበያ፡-
ይህን የፈጠራ ወሬ የመንዛት ተግባር ማን ሊፈፅመው ይችላል ለሚለው ጥያቄ መልሱ የህወሓት የበላይ ኣመራሮችና ደጋፊዎች ናቸው፤ ለዚህም ሁለት ኣበይት ኣመክንያዊ-ኩነቶች/Reasonable-Scenarios ኣሉ፤
ኣመክንያዊ-ኩነት ኣንድ፤
የዚህ ተግባር ኣንደኛው ኣመክንያዊ-ኩነት የሚመነጨው የኢህኣዴግ የውህደት ኣጀንዳና የኣዲሱ የብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ህወሓት ወደ ብልፅግና ፓርቲ ለመቀላቀል እግሩ እንደማያነሳና ልዩነቱ ይዞ እንዲሚታገል ኣሳውቆዋል፡፡ ይህም ተከትሎ በህወሓት ውስጥ ታላቅ ውጥረትና ልዩነት ነግሷል፡፡ የውጥረቱና የልዩነቱ መንስኤም ዶ/ር ደብረፅዮንና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.