የገቢዎች ሚኒስቴር በሳለፍነው የካቲት ወር ከ17 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8B%A8%E1%8C%88%E1%89%A2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B4%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%88%B3%E1%88%88%E1%8D%8D%E1%8A%90%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%89%B2%E1%89%B5-%E1%8B%88/
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በሳለፍነው የካቲት ወር ከ17 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።
 
ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግላጫ እንዳስታወቁት፥ በየካቲት ወር ብቻ 17 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብሰቧል።
 
አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ51 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ተናግረዋል።
 
ገቢው ከአገር ውስጥ ታክስና እና ከወጪ ንግድ ታክስና ቀረጥ የተገኘ መሆኑንም ነው ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተናገሩት።
 
በየካቲት ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ 10 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ የማሰባሰብ አፈፃፀም የተመዘገበ ሲሆን፥ ከወጪ ንግድ ታክስና ቀረጥ 7 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ሚኒስትሯ በመግለጫቸው አስረድተዋል።

Share this post

One thought on “የገቢዎች ሚኒስቴር በሳለፍነው የካቲት ወር ከ17 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.