የገቢዎች ሚኒስቴር በነሃሴ ወር ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ሰበሰበ

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%8B%A8%E1%8C%88%E1%89%A2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B4%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%8A%90%E1%88%83%E1%88%B4-%E1%8B%88%E1%88%AD-%E1%8A%A820-%E1%89%A2%E1%88%8A%E1%8B%A8%E1%8A%95/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት አመት በሰራቸዉ የንቅናቄ ስራዎች፣ የህግ ማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የህግ ማሻሸያ ስራዎች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።

ሚኒስቴሩ በወሩ 19 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ነው ከ20  ቢሊየን ብር በላይ የሰበሰበው። የእቅድ አፈፃፀሙም 102 ነጥብ 37% በመቶ ሆኗል።

15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከተሰበሰበበት አምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም 25 ነጥብ 45 በመቶ ብልጫ አለው።

በቀጣይም አመታዊ እቅዱ እንዲሳካ እና አገራዊ ገቢን የማሳደግ ራዕይው እውን እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ በበጀት አመቱ 248 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ነው ያቀደው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.