የጋምቤላ ክልል የክልሉን ከፍተኛ የፀጥታ ኃላፊዎች እና የከተማውን ከንቲባዎች ማሰናበቱ ተሰማ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131452

DW NEWS : ጋምቤላ፤ ከፍተኛ የፀጥታ ኃላፊዎች እና ከንቲባዎች ተሰናበቱ

የጋምቤላ ክልል የክልሉን ከፍተኛ የፀጥታ ኃላፊዎች እና የከተማውን ከንቲባዎች ማሰናበቱ ተሰማ። የክልሉ መንግሥት ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡዶል አጉዋ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት ባለሥልጣናቱ የተሰናበቱት በክልሉ በተለያዩ ጊዜዎች ከሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው።
አቶ ኡዶል እንደሚሉት ሰሞኑን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ፣ የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ እንዲሁም የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ ከሥራቸው ተነስተዋል።«ሰሞኑን የፀጥታ ችግር ነበረ እና በዚያች ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የመሪ ድርጅቱ የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴም ማዕከላዊ ኮሚቴም፤ በየደረጃው ገምግሞት የሰጠው አቅጣጫ አለ።
የክልሉን የሰላም እና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊውን ከቦታ እንዲነሱ አደረገ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩንም ከቦታቸው እንዲነሱ አደረገ።»አቶ ኡዶል ለባሕር ዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን በስልክ እንደገለፁት በተነሱት ኃላፊዎች ቦታ ሌሎች መመደባቸውን እና ለጋምቤላ ከተማ ክንቲባነትም እስከ ቀጣዩ ምርጫ የሚያገለግሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሁለት ከንቲባዎች ተመድበዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.