የጋሞ የአብሮነት እና የሰላም አባቶች እና ወጣቶች ጎንደር ገብተዋል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/202907

የጋሞ የአብሮነት እና የሰላም አባቶች በጎንደር! (አብመድ) 
የጋሞ የአብሮነት እና የሰላም አባቶች እና ወጣቶች ጎንደር ገብተዋል፤ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል፡፡

ከደቡብ ጫፍ እስከ ሰሜን ጫፍ የፍቅር ዥረት ፈስሷል። ሕዝቡ ሁሉ በፍቅር ዥረት አንጀቱ ርሷል። የኢትዮጵያዊያን ፍቅር ለይስሙላ አይደለም።
ከልብ የመነጨ እንጂ። በምንጮቿ ብዛት የተነሳ አርባ ምንጭ ከተባለችው ከፍቅር ከተማዋ ከጋሞዎች ምድር የተነሱት የፀብ እሳት አብራጅ ውሃዎች፣ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ሌላኛው የፍቅር መገኛ አማራ ምድር ገብተዋል። ደጉ የአማራ ሕዝብም ቅኖቹን እንግዶች በየመንገዱ ቄጠማ እየነሰነሰ፣ ከሚበላው እያጎረሰ፣ በባሕል ሸማ እያላበሰ በየመንገዱ እየተቀበለ ሸኝቷቸዋል። አማራ ለወዳጁ ፈትፍቶ ያጎርሳል፣አቅፎ ያንተርሳል፣ጥበብ ሸማውን ያለብሳልና። እንደ ዐይኑ ብሌን እየሳሳም እንግዳውን ቤቱ ያለ ያህል እዲሰማው ደርጋልና፡፡ ይህ የሕዝቡ መልካም እና ዘመን ተሻጋሪ እሴት ነው፡፡
የጋሞ ሽማግሌዎች ትናንት ስለፍቅር ተንበረከኩ፣ የተደገሰውን የፀብ ድግስም ተጠጥቶ ሳያሳከር፣ ተበልቶ ሳይመርዝ በእጃቸው በያዙት ለምለም ሳር አከሸፉት። ኢትዮጵያዊያንም ስለሽማግሌዎቹ ብዙ ነገር አሉ። ጉዳዩ ለትውልዱ አዲስ ሆኖ እንጂ ይሄስ በቅርብ የመጣ ስርዓት አልነበረም። ከቀደሙት የቀደመ ነው። የሀገርና የወገንን በሽታ ያከመ ጥንታዊ ነው የጋሞ የሽምግልና ስርዓት። ከጋሞዎች ጋር አብሮ የተፈጠረ እንደሆነም ይነገርለታል።
ዓለም ያየውን ሁሉ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው አይተውታል። ደራሲያን፣ ፀኃፈ ተውኔት፣ ገጣሚያን፣ ዘማሪያን፣ ዘፋኞች… ሁሉም በየሙያቸው ስለኢትዮጵያ ተናግረዋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ከተነገረው ታሪኳ ይልቅ ያልተነገረው ይልቃልና
“ጥንትም ላያልቅላት ምድሩ ላይነካ፣
ስትጨልፍ ዋለች ዓባይን በማንካ::”
እንዳሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ተቀመሰ እንጂ አልታዬም። ተጀመረ እንጂ አልተጨረሰም።
Image may contain: 2 people, people on stage, people standing and outdoor
በኢትዮጵያ ምድር በደቡቡ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.