የጋቦኑ ፕሬዚዳንት ምክትላቸውንና የደን ሚኒስትሩን ከሀላፊነት አነሱ

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8B%A8%E1%8C%8B%E1%89%A6%E1%8A%91-%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%8B%9A%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%89%B5%E1%88%8B%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8B%B0%E1%8A%95/

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋቦኑ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ  የሀገሪቱን ምክትል ፐሬዚዳንት እና የደንና የአካባቢ ሚኒስትሩን ከሀላፊነት ማንሳተቸው ተነገረ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ፕይራ ክላቬር ማጋንኛ ሞሳቩ እና የደን እና የአካባቢ ሚኒስትር ጉያ ቤርትራንድ ማፓንጎው ከሃላፊነት የተነሱት ከውድ እንጨት የህገ ውጥ ዝውውር ጋር ሳይያያዝ አይቀርም ተብሏል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱና ሚኒስትሩ በምን ምክንያት ከሃላፊነት እንደተነሱ ሳይታወቅ በፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ የመሰናበቻው ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተነግሯል፡፡

በፕሬዚዳንቱ በሚፀድቀው የደንና አካባቢ ሚኒስትር ቦታ ላይ እስከአሁን ድረስ የተሾመ ሰው እንደሌለ ነው የተነገረው፡፡

የደን እና የአካባቢ ሚኒስትር ጉያ ቤርትራንድ ማፓንጎው በመጥፋት ላይ ያለና ውድ የሚባለውን ኬቫዚንጎ እንጨት በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ተጠርጥረው በሲቪክ ማህበራትና ሚዲያዎች ከስልጣን እንዲወርዱ ጫና ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዜራ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.