የግልፅነት (ፕሮስትሮይካ) አርክቴክት (ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር )

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/44774

ካለፈው የቀጠለ የመጨራሻው ክፍል

ኢት-ኢኮኖሚ           /ET- ECONOMY

 ከህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም! የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ!!!›› አርክቴክቱ ዶክተር አብይ አህመድ የወንድም ልጅ ማሙሽ መታወሻ ትሁን! ሲያወጉኝ ከዛ ህልቆ መሳፍርት ወጣቶችን ለሞት የዳረገ ጦርነት ወያኔ በወንጀል ተጠያቂ፣ ያለቁ የደሃ ልጆች ናቸው!!! 

የፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ቴሌቪዝንና ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕራይቬታይዝ ይደረጉ፣!!!

የኢትዮጵያ የፖለቲካና ኢኮኖሚ አርክቴክት ወጣቱ ዶክተር አብይ አህመድ በሃገራችን በግልፅነት የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ አስተዳደራዊ መወቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ዴሞክራሲን ምርኩዛቸው፣ የፕሬስ ነፃነትን ኪታባቸው፣ ግልፅነትን ሃይማኖታቸው አድርገው ረጅሙን ጉዞ ለመሾፈር መሪውን ይዘዋል በእሳቸው አምኖ ከመርከቡ የገባ ህልቆ መሳፍርት ህዝብ ሌላው ሙሴ፣ ሌላው ሚካኤል ሰርጌቪች ጎርባቾቨ እያላቸው የግልፅነት (ፕሮስትሮይካ/Perestroika አራማጅ እያሉ ያሞካሹታል፡፡ ወጣቱ አርክቴክት የፖለቲካ ኢኮኖሚ የህሊና ግዝፈትና ምጥቀት፣ የሃሳብ የበላይነት፣ የማመንና የማሳመን ችሎታ፣ የፈሪሃ እግዜብሄር እሴቱ፣ የምህረት፣ የእርቀ ሠላም፣ የፍቅር፣ የሠላም ግልፅ መርህ፣ ፍርሃትን ድል የነሣ ኢትዮጵያዊ መሪ ለመሆን አስችሎታል፡፡ ዘመኑ የመደመር ነው፣ ስልጣን የህዝብ ነው፣ ዘመኑ የእውቀት እንጅ የኃይል አይደለም፡፡ ዘመኑ የዴሞክራሲ እንጅ የአንባገነንነት ዘመን አይደለም፡፡ መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣  መከላከያ ሠራዊቱና ደህንነቱ የሃገርና የወገን ሃሌንታ ሆኖ በሳይንሳዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጅ እየታገዘ በዘለቄታ ይቀጥላል፡፡ የዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣቶች እቺን ደሃ ሃገራችንን ወደ ታላቅ የሥልጣኔ ማማ እንደሚያወጦት አያጠያይቅም፡፡ መሣሪያ ነካሹ የእኛ ትውልድ፣ ቦንብ ታጣቂው የእኛ ትውልድ፣ ዝናር በቅፊ የእኛ ትውልድ ለፊልም ትወና ካልሆነ አትጠቀሙበት እኔ ቦድሜ ከያዘው ሠራዊት ጋር የነበርኩ የወንድሜ ልጅ ማሙሽ የሞተው እዚያ ነው፣ ማሙሽንና ብዙ ጎደኞቼነ የቀበርኩ እዚያ ነው!!! በዛ ይብቃ! መቼም የትም አይደገም!!! Nevere and ever againe!!! ይለናል ሌተናል ኮነሬል ከቁንፅል እድሜው ተመክሮው፣ በእኛ የፖለቲካ ቁማር ስንትና ስንት ደሃ ልጆች በጦርነት እንደተማገዱ ብዙ መፅሃፍ ፅፎ ልምዱን እንደሚካፍለን ጥርጥር የለንም፡፡ የህሊና ልዕልና የሰው ልጆችን የሚገዛ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት ችግራችንን እንድንፈታ፣ እንጅ የጦር መሣሪያና በኃይል የመፈታት አባዜ ዘመን ያለፈበት በመሆኑ፣ በኢትዮጵያችን ታሪክ በሙዚየም ተቀምጦ፣ በብረት መጋረጃ መዘጋቱን አብስሮል፡፡ በሶብየት ህብረት  ሚካኤል ሰርጌቪች ጎርባቾቨ የግልፅነት ፖሊሲ ያልተዋጠላቸው መሣሪያ ነካሽ የመከላከያ ሠራዊት መፈንቅለ መንግሥት በህዝባዊው ምክር ቤትና በመሪው ጎርቦቾቨ ላይ ባደረጉ ጊዜ የልሲን አይሞከርም ብለው ጎርቦቶቨን ታደጉ፣ ኩዴታውም በህዝብ ተጋድሎ ከሸፈ፡፡ የወያኔ/ኢህአዴግ ከዚህ መፈንቅለ መንግሥት ቢማር መልካም ነው እንላለን ህዝባዊው ዴሞክራቲክ ጋርድ በወጣቶች የተገነባ ህብረ ብሄራዊ ኃይል የአርክቴክቱን አንድ ትዕዛዝ ብቻ እንደሚጠብቅ ‹‹ወያኔ ቤት ጥይት፣ ህዝብ ቤት ክብሪት አይጠፋም!!!›› ይላችሆል፡፡ የወያኔ /ኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሴረኞች ሴራ ውስጥ እንደማይገቡ ለሃገርና ለወገናቸው የገቡት ቃል ኪዳን መጠበቃቸውን ግን አንጠራጠርም!!!         

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ‹‹የኢትዮ ቴሌኮም፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎ እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የሆቴልና የተለያዮ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ትልቁን የአክሲዮን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ ተወሰነ፡፡››  23 ግንቦት 2010ዓ/ም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፡፡  መንግሥታዊና የፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ፕራይቬታይዝ  መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡በመንግሥት ውስጥ መንግሥት!!! (A State within a State)የፓርቲ ሚዲያ ነው!   የመንግሥታዊ ልማት ዘርፎች ብድር  ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 42.0 በመቶ ሆኖል፡፡ በ2008ዓ/ም የውጭ ዕዳ ክፍያ  አንድ ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የወለድ ክፍያው በዓመት ከ350 ሚሊዩን ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ በ2009ዓ/ም የውጭ ዕዳና የወለድ ክፍያ 1.5 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 እስከ 50 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡ ሆኖም መንግሥት 24.7 ቢሊዮን ዶላር እዳ ብቻ እንዳለብን የተነገረን ሃሰት ነው፡፡ ወያኔ ሃገሪቱን  በእዳ ወጥመድ ውስጥ ከቶ ገንዘቡን ዘርፎል፣ አሽሽቶል፡፡ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ መንግሥት None concessional loan ብቻ እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር በታች እንዲበደሩ ማስጠንቀቂያ ሠጥተዋል፡፡ ሃገሪቱ ባለባት ብድርና የእዳ ጫና ምክንያት  የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎ እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የሆቴል ለቻይና መንግሥትና የወያኔ ኢፈርትና ሌሎች አበዳሪ ድርጅቶች በፕራይቬታይዤሽን ከመደረጋቸው በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎች የንግድ ቴሌቪዝንና ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕራይቬታይዝ እንዲደረጉ ለህዝብ በአክሲዮን እየጠየቅን የፕሬስ ነፃነት፣ የዴሞክራሲያዊ መብቶች መብታችንን ለመጎናፀፍ በሰላም መታገል ይኖርብናል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምላሳዊ ጋዜጠኞች የንግድ ቴሌቪዝንና ሬዲዮ ጣቢያዎች ፕራይቬታይዝ ይደረጉ፣ መንግሥታዊ የፌዴራልና የክልል መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዝን፣ ሬዲዩና ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች ለግሉ ዘርፍ በአክሲዮን ይሸጡ፡፡ ነፃ ፕሬስና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ነፃነት የሚረጋገጠው አድርባይ ምላሳዊ ጋዜጠኞች ተወግደው የህዝብ ልጆች ንብረትና ኃብት ሲሆኑ ብቻ ነው፣ ሙስና ሌብነት ከኢትዮጵያ ምድር የሚጠፋው፡፡ ነፃ ጋዜጦችና መፅሄቶች እንደአሸን እንዲፈሉ አፋኙ የፕሬስ ህግ፣ ፀረ-ሽብርተኛነት ህግ በአፋጣኝ እንዲነሳ እንታገል! ሀገራቸውን በወያኔ አገዛዝ ጥለው የወጡ ጋዜጠኞች  ተመልሰው እንዲሠሩ መጋበዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የክልል ብሮድካስት ባለሥልጣን የንግድ ካንፓኒዎች፣  የክልል መንግስታት የፓርቲ የንግድ ብሮድካስት ካንፓኒዎች የትግራይ ኢፈርት ፣ የአማራ ጥረት፣ ኦሮሚያ ቱምሳና የደቡብ የክልል ወንዶ የመገናኛ ብዙሃን የፓርቲ ቢዝነስ ድርጅቶች ፈጥረዋል፡፡ የክልል መንግስታት ብሮድካስት ባለሥልጣን የንግድ ካንፓኒዎች ውስጥ 1ኛ/ ሜጋ ፓብሊሽንግ 2ኛ/ ዋልታ መረጃ መዕከል 3ኛ/ ፋና ሬዲዩ ያካትታል፡፡ የፌዴራል መንግስት ዘርፍ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የንግድ ኢንተርፕራይዝ የህወሃት/ኢህአዲግ ‹‹የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› በመባል የሚታወቁት ውስጥ የሜጋ ፓብሊሽንግ፣ ዋልታ መረጃ ማዕከልና ፋና ሬዲዩ ይገኛሉ፡፡ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎች የፓርቲ ቢዝነስ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ፕራይቬታይዥሽን ኤጀንሲ (publishing and broadcasting) ተቆማትን በርካሽ የተሸጠላቸው የህዝብ ኃብት ዘረፋ የተቆቆሙ ድርጅቶች ናቸው፡፡

1ኛ/ ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ (Mega Publishing Enterprise) ኩራዝ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ በፕራይቬታይዥሽን ኤጀንሲ ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 35ቱን ማለትም 38.5 በመቶውን ድርሻ 13,031,048.06 ሚሊዮን ብር የገዛ ህወኃት ኢፈርት ድርጅት ነው፡፡ የኩራዝ መጽሃፍት ሱቆችና ቢዝነሶች በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ ዋና ዓላማ በሃገሪቱ የአሳታሚነት፣ የህትመት፣ የመዝናኛና የማስታወቂያ  ስራዎች ከግሉ ዘርፍ ባለሃብቶች ሥራ እየተሸማ ዘርፍን ለመቆጣጠር በቅቶል፡፡ ሜጋ ኢንተርፕራይዝ ከፌዴራል የትምህርት ሚኒስቴር ብዙ የትምህርት ቤት መፅሃፍቶች እንዲያትም ያለጨረታ በማሸነፍ በዘርፉ የተሰማሩ ማተሚያ ቤቶች ከጨዋታ ውጭ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ለናሙና በደቡብ ክልል በሜጋ ታትሞ በህዝብ የተቃጠለው መፅሃፍት  በብዙ ሚሊዩን ብር ወጭ ወጥቶበት እንደነበረ ልብ ይበሉ፡፡ ሜጋ  ኢንተርፕራይዝ  በአዜብ መስፍን ዋና ስራ አስኪያጅነት ይመራ ነበር፡፡ ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ በ1995እኤአ በ13ሚሊዩን ብር ኩራዝ ፓብሊሽንግ ድርጅትን ከ35 መደብሮቹ ጋር እንደገዛ ልብ ይበሉ፡፡ ሜጋ ኢንተርፕራይዝ ድርጅት ሲጀመር የአራቱ ድርጅቶች የህወኃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን የጋራ የንግድ ድርጅት የነበረ ሲሆን ከመዳፋቸው ፈልቅቀው ወያኔዎቹ ንብረታቸው እንዳደረጉት ይታወቃል፡፡  ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ በፕራይቬታይዤሽን በአክሲዮን ለህዝብ መሸጥ አለበት እንላለን፡፡ 

2ኛ/ ዋልታ መረጃ መዕከል (Walta Information Centre (WIC)፣ ዋልታ መረጃ መዕከል፣አስቀድሞ ዋልታ የዜና ኤጀንሲ ይባል ነበር፡፡ በ1996 እኤአ ዋልታ መረጃ መዕከል በሜጋ ኢንተርፕራይዝ ሥር ተደራጀ፡፡ ዋልታ ብቸኛው የሃገር ውስጥ ተወዳዳሪ በመሆን የኢትዩጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ድርጅት በመሆን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዜናዎች በመሸጥ መተዳደር ጀመረ፡፡ ዋልታ መረጃ መዕከል፣ በመላ ሃገሪቱ መረቡን በመዘርጋት ሪፖርተሮቹን ሰየመ፡፡ ዋልታ በኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ በሼር ካንፓኒ የተቆቆመ ካንፓኒ ነው፡፡   ዋልታ መረጃ መዕከል፣ በፕራይቬታይዤሽን በአክሲዮን ለህዝብ መሸጥ አለበት እንላለን፡፡

3ኛ/ ፋና ሬዲዩ (Fana Radio)ፋና ሬዲዩ የህወሃት/ኢህአዴግ ሬዲዩ በመሆን ጫካ እያሉ ያገለግል የነበረ በደርግ አገዛዝ  ዘመን የተቆቆመ የህወሃት የሬዲዩ ጣቢያ ነበር፡፡ ደርግ ከወደቀ በኃላ በሽግግር መንግስት ዘመን ፋና ሬዲዩ ስርጭቱን ቀጠለ፡፡ ፋና በሬዲዩ የግል ንግድ ዘርፍ ስርጭት ከሌሎች የግል ሬዲዩ ጋር ሆኖ ፍቃድ ተሰጠው፡፡  ፋና ሬዲዩ/ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ፕሮግራሞች በኮንትራት በመስራት ለተለያዩ ክልላዊ መንግስቶች ለሱማሌ፣ለኦሮሚያና ለአፋር በኮንትራት በመስራት ዳጎስ ያለ ጥቅም አገኘ፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጎን ፋና ሬዲዮ በ400 ሚሊዮን ብር ከባንክ ተበድሮ የገነባው ህንፃ ዋቢ መረጃ ነው፡፡ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች በሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ውስጥ የተወረሱ ኃብቶች በመቆጣጠር ኢፈርት በትግራይ፣ ጥረት በአማራ፣ ቱምሳ በኦሮሚያና ወንዶ በደቡብ ክልሎች ውስጥ እየተንሰራፋ ይገኛሉ፡፡ የኢትዩጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የኢኮኖሚ እኩልነት በምን ላይ የተመሠረተ ይሆን!!! የተወሰኑ ብሔሮች ሌሎቹን ብዙሃኑን የሚበዘብዙበትና የሚጨቁኑበት ሥርዓት መተከሉን ማንም ህሊና ያለው የሚገነዘበው ነው፡፡ ለአለፈው ሃያ አራት ዓመታት፣ ኢፈርት የአንበሳውን ድርሻ ሲያገኝ፣ ጥረት ሙዳ ሥጋ፣ቱምሳና ወንዶ ቅንጣቢ ሥጋ የደረሳቸው ይመስላሉ፡፡ ለሌሎቹ የብሄር ብሄረሰቦች  ቀን በአመት አንዴ ይከበርላቸዋል፡፡ ፋና ሬዲዮ በፕራይቬታይዤሽን በአክሲዮን ለህዝብ መሸጥ አለበት እንላለን፡፡

‹‹ ፋና ቴሌቪዥን፣ ከንግድ ባንክ 400 ሚሊዮን ብር ተበድሮ የተቋቋመው ፋና ቴሌቪዥን በ350 ሚሊዮን ስቱዲዮ ገንብቶ ለምርቃት በቅቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ይህንን ያህል ገንዘብ የተፈደቀው በአቶ በረከት ስምኦን ትዕዛዝ ነበር፡፡ የኤፈርት ንብረት የሆነው ፋና ወደ ቴሌቪዥን ከመቀላቀሉ ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ለምሳሌ ለፈታ ሾው 500 ሺህ ብር ሲሠጥ ለተለያዩ ድራማ ፕሮዲውሰሮች ደግሞ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እየሠጠ መሆኑን ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋና ስራ አስኪያጁ አቶ ወልዱ ይመሠል ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቀዋል ፡፡ በተለይም ከአዜብ መስፍን ጋር ባላቸው ትስስርና ኔትወርክ ሲታሙ ቆይተዋል፡፡ ፋና ከፍተኛ ገቢ ያለው ድርጅት ሆኖ ሳለ አንድም ቀን ኦዲት ተደርጎ አያውቅም፡፡ ይህ ደግሞ የወልዱንና የአዜብን ዝምድና ያጠናከረ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በተከናወነው የአዲስአበባ ሕወሐት አባላት ግምገማ የሠላ ሒሥ ከተሠጣቸው ሠዎች አንዱ አቶ ወልዱ ነበሩ፡፡ ከግምገማው በኃላም ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ከተሠጣቸው 6 ሠዎች አንዱ ለመሆን በቅተዋል፡፡ በነገራችን ላይ በአቶ ወልዱና በምክትላቸው የብአዲኑ ብሩክ ከበደ መሐከል ከፍተኛ ሽኩቻ ከተፈጠረ መቆየቱን ምንጮቻችን ጨምረው ነግረውናል፡፡››3 ከሱማሌው ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኤሊ ብዙ ሚሊዮን ብር በሙስና የተቀራመቱ ደም መጠጭ ጋዜጠኛ ተብዬዎች ብቃትና ቁመና በአባባ ታምራት ወያኔ ካልሆነ በሓሳብ የዘቀጡ የእንግዴ ልጆች ቦታ የላቸውም፡፡ 

{I} የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች  የመንግሥት ብሮድካስት ድርጅቶች፤በኢትጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሥር በህወሓት/ ኢህአዴግ የሚሽከረከር {1} የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በኦሮሚያ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በኦህዴድ የሚዘወር {2} የኦሮሚያ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት፣ በኦሮሚ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በኦህዴድ የሚዘወር {3} የድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት፣ በድሬ ዳዋ አስተዳደር  ሥር በህወሓት/ ኢህአዴግ የሚሽከረከር {4} የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ፣ በአማራ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በብአዴን የሚዘወር {5} የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር  ሥር በህወሓት/ ኢህአዴግ የሚሽከረከር

{6} የደቡብ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት፣ በደቡብ ኢትዩጵያ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥር በደኢህዴድ የሚዘወር {7} የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት፣ በትግራይ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በህወሓት የሚዘወር {8} የሀረሪ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት፣ በሃረሪ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በሃዴድ የሚዘወር {9 }የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ፣ በሶማሌ  ብሄራዊ  ክልላዊ መንግሥት ሥር በሶህዴድ

{10} የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ፣…በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥር በቡህዴድ የሚዘወር

{11} የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በኢትጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሥር በህወሓት/ ኢህአዴግ የሚሽከረከር {12} የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣በኢትጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሥር በህወሓት/ ኢህአዴግ የሚሽከረከር መገናኛ ብዙሃን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ንግድ ዘርፍነት መላቀቅ ይኖርባቸዋል፣ ሃገሪቱ ህግም አይፈቅድ፡፡

{II} የግል ቴሌቪዥን ብሮድካስት ፍቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች፤ {1} ፋና ብሮድካስቲንግ  ኮርፖሬሽን {2} ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል {3} አርኪ ብሮድካስቲንግ ስርቪስ ኃ.ተ.የገ. ማ {4} የቃና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን {5} የኢኤን ኤን  ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን {6} ናሁ ቲቪ፣  {7} ዋልታ ቲቪ {8}  ኢኤንኤን ቲቪ፣  {9} ፋና ቲቪ፣ ኢኦቲሲ ቲቪ፣ ድምፂ ወያኔ  የባህር ማዶ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ  ብሮድካስት፤ {1} ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቨዥን (ኢሳት) {2} የጄቲቪ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን {3} ሌቲቪ ኢትዮጵያ፣ በቀጥተኛና ቀጥተኛ ባሆነ መንገድ የፖለቲካ ፓርቲ ንብረት የሆኑ የመገናኛ ብሁሃን ድርጅቶችንም ይጨምራል፡፡

{III} የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የግል መገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች (የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ብሮድካስቲንግ ፍቃድ የተሰጣቸው {1} ሸገር ኤፍ ኤም102.1 ወ/ሮ መኣዛ ብሩና አበበ ባልቻ {2} ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱና ዘሪሁን ተሸመ {3} ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን {4} ድምፂ ወያነ ትግራይ ሬድዮ{5} አፍሮ ኤፍኤም 105.3 {6} ዓባይ ኤፍኤም 102.9 {7} ብስራት ኤፍኤም 101.1 {8}ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል {9} አሐዱ 94.3 በኤዲስቴለር ትሬዲንግ ኃ.የተ.የገ.ማ {10} አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ {11} ሉሲ 107.8 በዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ /ኤፍ ኤም ሠራዊት ፍቅሬ፣ ሸዋፈራሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ  ፍቃድ አግኝተዋል ይባላል፡፡ ስናውቃቸው መሰረተ ደሃ፣ ሳናውቃቸው በአንድ ጀንበር የኤፍ ኤም ሬዲዬ ባለቤቶች የሆኑ ወያኔ የፈለፈላቸው ሬዲዬ ጣቢያዎች ሃብትና ንብረት የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፣ ጉዳዩ ለህዝብ ሲቀርብ ይህን ሃብትና ንብረት እንዴት እንዳገኙት መረጃችንን ሰድረን እንቀርባለን፡፡ ምላሳዊ ጋዜጠኞች የወያኔ አፋሽ አጎንባሽ፣ እውቀት አልባ ዝግምተኞች ከእንግዲህ ቦታ የላቸውም፣ የድሮውን የፕሬስ አሻጥር ሙዝየም አስጎብኝ  ከመሆን ሌላ፡፡  

የባህር ማዶ ሬዲዮ ጣቢያ ፕሮግራም ሥርጭት፤ {1} ቪኦኤ፣(ቮይስ ኦፍ አሜሪካ)የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ከአሜሪካ ሀገር በአማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል {2} ዶቼቬሌ፣ የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ ከሀገረ ጀርመን  በአማርኛ ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል {3} ሞስኮ፣ የሞስኮ ሬዲዮ ጣቢያ ከሶቭየት ህብረት በአማርኛ፣  ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል ነበር {4} በሞቃዲሾ ሬዲዮ ጣቢያ ከሱማሊያ በአማርኛ፣ ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል ነበር {5} ቫቲካን ሬዲዮ  ጣቢያ በአማርኛና፣ ትግርኛ ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል {6}ፍኖተ ዴሞክራሲ {7}ኦሮሞ ሚዲ ኔትወርክ {8} ዋዜማ {9} ቢቢሲ፣የዓለም አቀፍ ዜና አውታርነት የሚታወቀው ብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ሬዲዮ ጣቢያ በአማርኛ፣ ኦሮምናና ትግርኛ  ቆንቆ ስርጭቱን ያስተላልፋል ቢቢሲ በዓለም አቀፍ 40 ቆንቆዎች አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ የ100ኛ አመቱን ኢዩቤልን በ2022 ለማክበርና አድማጮቱን ቁጥር ግማሽ ቢሊን ለማድረስ በመስራት ላይ ነው፡፡ ምስጋና ይገባችሆል፣ የጋዜጠንነት ስነምግባር በማስተማር መረጃ ለጠጠማው የሃገራችን ህዝብ ተስፋ ፈንጣቂ፣ የፕሬስና የጋዜጠኝነት ፋና ወጊ ሆናችሁ ከዘመን ዘመን አሻግራችሁናልና!!!   

{VI} የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የህትመት ውጤቶች፤{1}  ሪፖርተር ጋዜጣ {2} ፎርቹን ጋዜጣ {3} ካፒታል ጋዜጣ {4} አዲስ አድማስ ጋዜጣ {5} ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ {6} ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ {7} የኛ ፕሬስ ጋዜጣ {8} ሊግ ስፖርት ጋዜጣ {9} ኢንተር ስፖርት ጋዜጣ {10} ወርልድ ስፖርት ጋዜጣ {11} የቀለም ቀንድ ጋዜጣ {12} ህብረ ብሄር  መፅሄት {13} ቁም ነገር  መፅሄት {14} ቤስት ስፖርት መፅሄት {15} ሸጊቱ መፅሄት {16} ንግሥት መፅሄት {17} ናሽናል ኮንስትራክሽን መፅሄት {18} ኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቨው መፅሄት {19} አዲስ ገፅ መፅሄት {20} ከ ሀ-ፐ መፅሄት {21} ፀሃይ መፅሄት {22} ሜዲካል መፅሄት {23} ፎከስ መፅሄት {24} አዲስ ስታንዳርድ መፅሄት {25} ጊዜ መፅሄት መንግሥታዊ ጋዜጦች፤ ወዘተ ናቸው፡፡ የሃገሪቱ መንግሥት ጋዜጦች የሆኑት {1} አዲስ ዘመን {2} ዘ ኢትዮጵያ ሄራልድ ወዘተ  መንግሥታዊ መረጃ በመንፈግ ለሪፖርተር ጋዜጣ በመስጠት ወያኔ ቱልቱላነት ታሪካዊ ጋዜጦቹ እንዲኮስሱ በማድረግ የተሰራው ታሪክ የማጥፋት የ27 ዓመት ታሪክ በቃ ሊባል ይገባል፣ ጋዜጦቹ ወደ ወርቃማው ዘመናቸው ዳግም ተደራጅተውና በበቂ የሠው ኃይል ተደራጅተው ዳግም እንዲያብቡ ማድረግ የታሪክ ኃላፊነት አለብን፡፡  

{V} የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ማህበራትን፤ {1} የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር {2} የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሴቶች ማህበር {3} የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞቸ ማህበር {4} የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር {5} የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር {6} ብሄራዊ የጋዜጠኛች ህብረት ዳግም በሃቅ የመደራጀት መብታቸው ይጠበቅ፡፡ ምላሳዊ ጋዜጠኞች የሚመሩት እነ አማረ አረጋዊ፣ ሚሚ ስብሃቱ፣ አበበ ባልቻ፣ ወዘተርፈዎች ወደ ታሪካዊ የፕሬስ ሙዚየማችሁ የምትከቱበት ዘመን መጥቶል፡፡ የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣት ጋዜጠኞች በእውቀትና ክህሎት ተደራጅተው ወጣቶቹን ሊያደራጅ፣ እውቀት ሊያቀስሙ፣ ሙያቸውን ሊያቆድሱ፣ የጋዜጠኝነት ሙያ በትምህርት የሚሠጥ፣ በጥናት ምጥቀት፣ በምርምር ስራዎች አስተወፅኦ በረከት ያላቸው ጋዜጠኞች ማህበራትን የማደራጀትና የመምራት ብቃት ይኖራቸዋል እንላለን፡፡ ሚዛኑ እውቀት ነው፡፡    

{VI} ድረ-ገጾች {1} አይጋ ፎረም {2} ኢትዮሚዲያ {3} ኢትዮጵያን ሪቪው {4} ዘ-ሃበሻ {5} አባይሚዲያ {6} ሳተናው ወዘተ ማህበራዊ ድረገጾች፤ ፌስቡክ፣ ቲውተር፣ ዩ ቲውብ፣ ሊንክድ ኢን ወዘተ አፈና አይካሄድባቸው፡፡ ላደረጋችሁት የአልሞት ባይ ተጋዳይ የጨለማ ዘመን ታሪክና ህዝብ ሲያስታውሳችሁ ይኖራል፡፡ ለድምፅ አላባው ወገናችሁ እልህ አስጨራሺ ትግል በማድረግ ላደረጋችሁት ትግል ልትኮሩ ይገባል፡፡

‹‹ፍሪደም ሐውስ፣ ኢትዮጵያ ከቻይና ተከትላ ከሶሪያ እኩል የኢንተርኔት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ላይ ገደቦችን በመጣል በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች አለ። የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ በተነሳበት ህዝባዊ ተቃውሞ በመደናገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን ችግሩን መፍታት ስለተሳነው ህዝባዊ ንቅናቄው ከዳር እስከዳር ተጋግሎ መቀጠሉ ይነገራል። በዚህም የተነሳ አገዛዙ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው የኢንተርኔት አገልግሎት በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ማቋረጡ ሲነገር በኦሮሚያም የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ከባድ እንደሆነባቸው ነው የሚነገረው። እንደዚሁም በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም አገልግሎት ማግኘት እንደሚያስቸግር የታወቀ ሲሆን ባጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡ መረጃ እንዳያገኝና እንዳይለዋወጥ በማድረግ ተቃውሞውን በሃይል ለመጨፍለቅ እየሞከረ መሆኑን ይነገራል። ሀገሪቷ በፖለቲካ ምክንያት ኢንተርኔት ስታቋርጥ ለመጀመርያ ጊዜ አለመሆኑን አዲስ እስታንዳርድ ዘግቧል። ጋዜጣው እንደዘገበው ከሆነ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት መጠቀም ከባድ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ በድረገጽ ነፃነት ‘Freedom of the Net’  ሪፖርት “የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት እንዲሁም 100% የኢንተርኔት ነጻነት የሌለበት” በሚል መስፈርት ተመዝና 86 ነጥቦችን በማምጣት ከሶሪያ እኩል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ከቻይና ቀጥላ ተቀምጣለች ብሏል።›› (ኢትዮጵያ ከቻይና በመቀጠል የኢንተርኔት ገደብ በመጣል ከአለም ሁለተኛ ተባለች አባይ ሚዲያ ዜና በአሰግድ ታመነ) የኢንተርኔት አገልግሎት የማግኘት ነጻነት አለመኖር በሃገሪቱ ፀረ- ዴሞክራሲው ኃይል ሴራ በመሆኑ ነገር አለ ማለት እንደሆነ ህዝቡ ከትላንት ልምዱ እንዲገነዘብ ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች ዴሞከራቲክ ጋርድ ለፕሬስና ዴሞክራሲያዊ ነጻነት ትግል ማበብ እንታገል፡፡

ለፕሬስ ነፃነት እንታገል!!!

ለዴሞክራሲያዊ ነፃነት እንታገል!!!

(ተፃፈ ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ/ም አብይ እባክህ የሞሙሽን ፎቶ ላክልን፣ ጦርነት በኢትዮጵያ ምድር ‹‹መቼም የትም አይደገም!!!›› በነማሙሽ ይብቃ ወጣቱ ትውልድ እንዲል አይከን ይሆናልና!!! ታላንት ማሙሽን አላዳንከውም፣ ዛሬ ግን ብዙ ማሙሾችን አድነሃልና ክብር ይገባሃል!!!)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.