የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራራ የአበበ ቦጋለ እና የቀበሮዋ ታሪክ!

Source: http://welkait.com/?p=12069
Print Friendly, PDF & Email

የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራራ የአበበ ቦጋለ እና የቀበሮዋ ታሪክ!

(በከፍያለው ጌጡ)

ከእለታት ባንድ ቀን አንድ በጣም የተራበች ቀበሮ የጽሃይን መጥለቅ በጉጉት ስትጠብቅ ውላ ልክ ጸሃይ እንደጠለቀች ከጉሬዋ ወጣ ራቧ ሳይደፋት አንድ ነገር አግኝታ ለመብላት መኳተን ጀመረች። የሚበላ ፍለጋ ስትወጣ ስትወርድ ድንገት አንድ ነገር ላይ አይኗ አረፈ። የወይን ዛፍ ላይ። ሙክክ ብሎ በስሎ የተንዠረገገ ወይን። ሆዷ እየጮኸ ምራቋ እየተዝረበረበ ወደ ወይኑ ዛፍ ቀረበች። አፏ በቻለው ልክ ቦትርፋ ለመዋጥ ወደ ዘለላው አንጋጠጠች። መድረስ አልቻለችም። ዘለለች አልቻለችም። ወይኑ ከቀበሮው ለመዳን ወደላይ ይሸሽ ይመስል ይበልጥ ስትዘል ይባስ ይርቃታል። በብሽቀት እና በራብ እየተቃጠለች ዘለለች። ዘለለች። ዘለለች። አልቻለችም።

ቀበሮዋም ወይኑ ዛፍ ስር ቆማ በድካም እና በቁጭት ስትተክዝ ከቆየች በኋላ ሙክክ ያለውን የወይን ዘለላ ቀና ብላ አይታ “ምን አለፋኝ እንዴውም ወይኑ እኮ ገና አልበሰለም” ብላ ኋላዋን ለወይኑ ዛፍ ሰጣ ማዝገም ጀመረች።

አበበ ቦጋለ

ግንቦት ሰባት በአበበ ቦጋለ በኩል የሰጠው “አማራው ጠንካራ ድርጅት ስለሌለው ነው አብረነው የማንሰራ” የሚለው ምላሽም ቁርጥ ቀበሮዋ ዘላ ዘላ አልችል ስትል “እንዴውም እኮ ወይኑ አልበሰለም” ያለችውን ይመስላል። በሻለቃ ዳዊት እና ዶክተር ጌታቸው በጋሻው በኩል የስንት አማራ ድርጅቶችን ደጅ ሲጠኑ እና ሲዘሉ ከርመው “ለምን ከአማራው ጋር አትሰሩም” ሲባሉ አቤ እንቆቆው” ምን ድርጅት አለና” ይልሃል። እንዳማሩ መሞት ወዴት ነው ሃገሩ ይላል አማራ እንዲህ አይነቱን ነገር ሲታዘብ።

ዳግማዊ ብአዴንን ለመፍጠር አይዘሉ፣ ሲዘሉ ከርመው እና አሁንም እየዘለሉ የአማራ ድርጅቶች የወይኑን ዘለላ ሲሆኑበት ላፕቶፑ ላይ የድርጅት ሎጎ ፈጥሮ “አማራ ወጣቶች ንቅናቄ” ሲል እና ሲያስብል የሚውል ድርጅት “ምን ጠንካራ የአማራ ድርጅት አለና አብራችሁ ስሩ ትሉናላችሁ” ሲል ስትሰማ ከመሳቅ ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል ጎበዝ።

እንዴው የኢትዮጲያ ፖለቲካ ግን መቼ ነው ከማጅራት መችዎች እጅ ወጦ እግዜርንም ህሌናቸውን በሚፈሩ ሰዎች እጅ የሚገባው!? የሌንጮ ለታው ድርጅት ስንት አባላት አሉት? የሲዳማ እና አፋር ንቅናቄዎች ሲዳማ እና አፋር በሚባሉ ህዝቦች ስም ከመተራታቸው ውጭ አባሎቻቸው አንድ አንድ ሊቀመንበር እና ማህተም ብቻ ነው። “ትለፊያታለሽ እንጅ አትከብሪያት” አለ አያ ሽቴ።

ለአቤ አባ ግርሻ አንድ ጥያቄ በመጠየቅ ልጨርስ፡-

ቀኝ አዝማች አቤ ለመሆኑ እንደ እናንተ በኤርትራ ምድር ያለው አዴሃን ያለው የታጋይ ቁጥር ከእናንተው ስንት እጥፍ ነው። ቀላል ዳሽ ሙላ ጥያቄ ናት። ለመመለስ አትቸገርም። ካልሆነ ሌላ ጊዜ እኔው እመልሰዋለሁ!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.