የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩና በአዲስ አበባ ላይ የጣሱት “ቀይ-መብራት”

Source: http://welkait.com/?p=11404
Print Friendly, PDF & Email

(አያሌው መንበር)

ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉዳይ በአይነኬ ሰዎች እየተወራ ሃሳብ ስንሰነዝርም ከበጎነት እንደማይታይ አውቃለው። ነገር ግን ይህንን ፈርተን ዝም ማለት ያለብን አይመስለኝም በማለት ባለፈው ሳምንት የማከብረው ሰው ያልኩትን ሰው ሀሳቡን ልሞግት ብቅ ብያለው።

ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ናቸው። እርሳቸውና ጓደኞቻቸው የሚናገሯቸው ንግግሮች፣ የሚፅፏቸው ፅሁፎች እኛ ልጆች ወይም ማንንም የማንወክል ሰዎች እንደምንፅፈው አይታይም። እናም ሁለመናው ይመነዘራል።

ዶ/ሩ ስለአዲስ አበባ በኢሳት ባቀረቡበት ዝግጅታቸው የፕሮግራሙ አላማ ባይገባኝም (ማዝናናት፣ ማሳወቅ፣ ማስተማር…የትኛውን አላማ እንደያዘ አላውቅም) ያልዳሰሱት ጉዳይ የለም። አዲስ አበባን ለምን አሁን ማንሳት ፈለጉ? የሚለው ጥያቄ አልተመለሰልኝም። በንግግራቸውም እንዲህ ይላሉ።

1. አዲስ አበባ የማናት የሚለው አጨቃጫቂ ነው ይሉና …”አዲስ አበባ የማን ናት? የፌደራል መንግስት?፣ የኦሮሚያ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዌች?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ዶ/ሩ እነዚህን ዝርዝሮች ሲጠቅሱ የአዲስ አበባ ጉዳይ ከህዝቦቿ አልፎ ወደ ባለቤትነት ክፍፍል ከመጣ #የእኔ ናት የሚለውን የታሪካዊም የነባራዊም ባለቤቱን አማራ ለምን ዘለሉት? የሚል መሰረታዊ ጥያቄን በመጠየቅ የግልሰቡ ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ ራስን ጥያቄ መጠየቅ ያሻል። አዲስ አበባ የሸዋ ግዛት የነበረች፣ በአማራ የተመሰረተች፣ አሁንም 56% ነዋሪ አማራ መሆኑ ይታወቃል። (ዳታውን ዶ/ሩም ባይቀበሉትም ተናግረውታል)።

2. የአዲስ አበባ የመጠሪያ ስም ጉዳይ “ሁለት መጠሪያዎች (ፊንፊኔና አዲስ አበባ እኩል እየሆኑ ነው) ሁለቱም አሳማኝ ናቸው፣ ሁለቱም ተቀባይነት ያላቸው ናቸው ብለውናል።

ዶ/ር ታደሰ ይህንን ሲሉ ማስረጃ እና ምንጭ አልጠቀሱም። አለመጥቀሳቸውን እንለፋቸው ቢባል እንኳን የአዲስ አበባ ስም የሌሌችን ፍላጎትና ብዙ መለኪያዎችን ሳያገናዝብ በመቀየሩ ትክክል አይደለም የሚለውን ብዙሃኑን ማህበረሰብ ያላገናዘበ ነገር ተናግረዋል።በተለይም ይህ ንግግር ግ7 ከህወሃት ጋር በዚህ ጉዳይ ተስማምቻለውና ወደፊትም አልቃወምም፤ እንደራደር የሚል አካሄድ እየሄዱ ነው ለሚባል ሀሳብ በር ከፋች ነው። በዚህም ህወሃት የወሰነው ነገር ትክክል ነው፤ ይህንንም ድርጅታቸው ይቀበላል ብለን እንድናምን ያስገድደናል።

3ኛው ጉዳይ የአዲስ አበባን የነዋሪ ስብጥር ውድቅ ለማድረግ የህወሃትን መረጃ ተቀባይነት የለውም ለማለት የሄዱበትና ቆየት ብለው ራሳቸው ያፈረሱት ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ 3.5 ሚሊዮን መባሉ አያሳምነኝም ካሉ በኋላ “ነዋሪውም ሁሉም የተመጣጠነ ማህበረሰብ አይደለም፤ በእኩል ነው የተውጣጣው ማለት አይደለም፤… እያሉ ይዘረዝራሉ። የቁጥሩ ጉዳይ እኔ ስንትም ይሁን ስንት ችግር የለብኝም። እርሳቸው 8 ሚሊዮን ወይም በኢትዮጵያ በከተማ ከሚኖረው ህዝብ 1/3ኛው አዲስ አበባ ይኖራል ብለዋል። እነ ጎንደር መቀሌ አዋሳ ባህር ዳር ደሴ ወዘተን የመሳሰሉ ከተሞች ሁሉም ቢደመሩ የከተማ ነዋሪው ሲለካ 1/3ኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው የሚለውን ለመቀበል ቢከብደኝም ማለቴ ነው። እዚህም ላይ የሄዱበት አላማ አልተገለፀም። የህወሃትን ሰነድ ላለመቀበል ቢሆን ኑሮ በኋላ ቅር እያላቸውም 56% አማራ፣ 19% ኦሮሞ፣ 16% ጉራጌ እያሉ ለማስረጃነት ባልተጠቀሙበት ነበር።))ጥያቄው ግን “ነዋሪው በእኩል ነው የተመጣጠነው ማለት አይደለም፣ ከፊሉ መጥቷል፣ ከፊሉ ወጥቷል ሲሉም ይጨምራሉ። ስለዚህ የመነሻቸውን ጉዳይ እዚህ ላይም እንድናስበው ያስገድደናል።

4ኛው እና መሰረታዊ የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር የብሄር ስብጥር ይሉና ማስረጃው ባያሳምነኝም “56% ከአማራ ክልል የመጣ ነው” ሲሉ ይገልፃሉ። በመሰረታዊነት የሚነሳው እና መታወቅ ያለበት አሁን አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር የአማራ እየኖረ ያለው ቀደምት አባቶቹ ከመሰረቷት ርስቱ እንጅ ከሰው ርስት መጥቶ አልሰፈረም።በምን ማስፈርት ነው “ከአማራ ክልል የመጣ” ተባሎ የሚገለፀው?

ዶ/ር ታደሰ ይቀጥሉና “19% ኦሮሞ፣ 16% ጉራጌ ነው” ይሉናል። ልብ በሉ ይህ ማን ማለት ነው? የአዲስ አበባ ኦሮሞ ከሌላ ቦታ የመጣ ሳይሆን ባለ ርስት፣ የአ.አ አማራ ግን ባለ ርስት ሳይሆን ከአማራ ክልል የመጣ ነው እያሉን ነው። ዶ/ር ታደሰ ብሩ እዚህ ላይ ድምፍቸውን ቀንሰውም ቢሆን አንዱ ሲመጣ አንዱ ሲወጣ ሲሉም ይናገራሉ። ይህ አካሄድ ነው እንግዲህ የዶ/ሩ መነሻን በደንብ እንድናጤነው የሚያስገድደን። እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን በወልቃይት ላይ ተፈትኖ የወደቀው ድርጅታቸው ግንቦት 7ም እንዲህ አይነት አቋን አለው ማለት ነው።እናም አቋሙን በአንድ በህዝብ ይወደዳል በሚባል አመራሩ በኩል አስነግሮ የህዝብ ስሜት እየለካ ነው ብለን እንድንወስድ እንገደዳለን። እርግጥ ነው በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ጉዳይ ሌላኛው የድርጅት አመራራቸው አስገራሚ ፅሁፍ ፖለቲከኞችን ሲያነጋግርን ነበር።አቶ ሙሉነህ ኢዮኤል “የዚህ ትወልድ ትልቁ ፈተና ኦሮሚያን መታደግ/ማስቀጠል” ነው በሚል ፅሁፋቸው ብዙ አነጋሮናል። በእርሳቸው እይታ ኦሮሚያ የምትባለዋ ህወሃት የሳላት ካርታን ጠብቀን ማስቀጠል በሚለው ሂደት ውስጥ አወቃቀሩ ትክክል አይደለም የሚለውን ሀሳብ ተቃውመው ይልቁንም አወቃቀሩንም እየተቀበሉ መሆኑ ነው። እናም ይህ ንግግራቸው በወቅቱ ብዙዎች ስለፃፉበት አሁን ምንም ማለትን አልሻም።

የዶ/ር ታደሰ አካሄድ የረገጠው ቀይ መብራት ድርጅታቸውን የበለጠ በስጋት እንድንመለከተው ያደርገናል። እውን እርሳቸውና ድርጅታቸው መመለስ የማይፈልጉትን የአ.አን ጉዳይ ዛሬ ለዚያውም በሀገር ቤት እንኳን ቁስሉን አሁን መነካካት የለብንም በተባለበት ሰዓት (አጋራቸው ሙሉነህ ኢዮኤል “የኦሮሚያን በአዲስ አበባ ላይ የሚኖረውን ጥቅም” ጉዳይ እንደርስበታለን ለጊዜው እንተወው ብለውን ነበር። ይህ ራሱ ብዙ ማለትን ያሻል) ዶክተር ታደሰ ታድያ ለምን ማንሳት ፈለጉት? አማራውን መጤ ሌላውን ነዋሪ ለማለትስ ያስደፈራቸው ምን ይሆን? ለጊዜው ዝም ያልነውን የአዲስ አበባን ጉዳይ እንድናነሳው ተገደናል። ሲጠቃለል የአማራ ህዝብ ለአዲስ አበባ መስራች እና ባለቤት እንጅ መጤ አይደለም።የአዲስ አበባ ማንኛውም ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጠው በነዋሪው ነው።

የባሌ ኦሮሞ ወይም የከንባታ ነዋሪ ስለ አዲስ አበባ መናገር ሲጀምር ግን በመሀል ሸዋ እና ዙሪያው ያለው አማራ ብቻ ሳይሆን የወልቃይት፣ የራያ፣ የመተከል አማራም እኩል መናገርም መወሰንም ይጀምራል።የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ በድርጅት አይመለስም።በግልሰብም አይለገስም።

((በተረፈ ከህወሃትም ከኦነግም ጋር መደራደር ይቻላል። ተቃውሞ የለንም ነገር ግን የአማራን ጥቅም ረግጦ ማለፍ አይቻልም። ከአማራ የለም እስከ አማራ መጤ ነውን እየሰሙ ያሉ የድርጅቱ አባል አማራዎች ዛሬስ ምን ይሉ ይሆን?)))

ሙሉውን ንግግር ከታች አያይዠዋለው።

 

Share this post

Post Comment