የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችና ቤተ እስራኤላዊያን ለተፈናቃዮች የ13 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8B%A8%E1%8C%8E%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%88%AD-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8A%90%E1%8B%8B%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD%E1%8A%93-%E1%89%A4%E1%89%B0-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%8A%A4%E1%88%8B/

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና በእስራኤል የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች (ቤተ እስራኤላዊያን) በጎንደርና በአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የ13 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለተፈናቃዮቹ 12 ሚሊየን 443 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በተመሳሳይ በእስራኤል የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ደግሞ 580 ሺህ ብር ድጋፍ እንዳደረጉ ነው የተገለፀው።

እንዲሁም ሲዲኤፍ ቢዝነዝ ግሩፕም ለተፈናቀሉ ዜጎች የ300 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረገ መሆኑን ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ አስታውቋል።

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር አማረ ክንዴ ለተደረገው ድጋፍ በተፈናቃዮች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አማረ እስከአሁን በተደረገው ድጋፍ የማሰባሰብ ሂደት330 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል።

በናትናኤል ጥጋቡ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.