የጎንደር ከተማ ፋኖዎች እና ወጣቶች በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎችን በማረሚያ ቤት በመገኘት እንኳን አደረሳችሁ ማለታቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም…

የጎንደር ከተማ ፋኖዎች እና ወጣቶች በእስር ላይ የሚገኙ ፋኖዎችን በማረሚያ ቤት በመገኘት እንኳን አደረሳችሁ ማለታቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጎንደር ከተማ ከሚገኙ ፋኖዎችና ወጣቶች ለአዲስ ኤክስኘረስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ለወራት በእስር ላይ የሚገኙትን ፋኖዎችን ማረሚያ ቤት በመሄድ እንኳን አደረሳችሁ በማለት መጠየቃቸውን አስታውቀዋል። በጎንደር ከተማ የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው ፋኖ ሙላት አድኖ ለአዲስ ኤክስኘረስ እንዳለው የደመራ መስቀል በዓልን መክንያት በማድረግ ከወራት በፊት ለእስር የተዳረጉ ፋኖዎችን በማረሚያ ቤት በመገኘት አጋርነታችንን እና እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ያለመ ዝግጅት መሆኑን ተናግሯል። በሀገሬ አሜሪካ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ መረዳጃ ማህበር ፋውንዴሽን ድጋፉን እንድንሰጥ የገንዘብ ድጋፍ አድርጎልናል ያለው ፋኖ ሙላት ለዚህም ምስጋናውን አቅርቧል። በጎንደር ለሚገኙ የህሊና እስረኞች ድጋፍ እንደተደረገው ሁሉ በተመሳሳይ በባህርዳር ሰባታሚት በእስር ላይ ለሚገኙ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ድጋፍ እንደተደረገ ጨምሮ ለአዲስ ኤክስኘረስ ገልጧል። በድጋፉም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ እና በጎንደር ባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ለሚገኙ ለፋኖዎች እና ለከፍተኛ የጦር መኮንኖች ለበዓል መዋያ የሚሆን የበሬ ሰንጋ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው አዲስ ኤክስፕረስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply