የጎንደር ጉዳይ – (ክፍል ፩)

Source: http://welkait.com/?p=9422
Print Friendly, PDF & Email

(ከአቻምየለህ ታምሩ)

ጎንደር

ፋሽስት ወያኔ የዐማራ ተጋድሎና የዐማራ በኢትዮጵያዊነቱ በአንድነት የመነሳት መንፈስ ማዕከል የሆነውን ጎንደርን ለመከፋፈል እቅድ አውጥቶ፣ ቀን ቆርጦ እየሰራ እንደሆነ በሎሌው በሆዳሙ ዐማራ ገዱ አንዳርጋቸው በኩል ከሰሞኑ ነግሮናል። ሎሌው ገዱ አንዳርጋቸው ወያኔ ብአዴን ብሎ ባቋቋመው የሕወሓት ነውረኛ ድርጅት መዋቅር ውስጥ እነ ክፍሌ ወዳጆ ባረቀቁት የወያኔ ሕገ መንግሥት «የዐማራ ክልል» በተባለው የወያኔ መፈንጫ ሜዳ በርዕሰ መስተዳደርነት የተሰየመ ሎሌ ነው። እጀ መድሀኒቱ ሐኪም ሰማዕቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከዐማራ አንጻር ፋሽስት ወያኔ ያዘጋጀውን ሕገ አራዊት በሎሌነት ካረቀቁት መካከል ቀዳሚ የሆነውን የብአዴኖቹን የገነት ዘውዴና የዳዊት ዮሐንስን ዘመድ ክፍሌ ወዳጆን «ሆዳም ዐማራ» ሲሉ ይጠሩት ነበር።

እውነት ነው ነውረኛው ክፍሌ ወዳጆ ጭድ የሚበላ የወያኔ አጋሰስ ነበር። ክፍሌ ወዳጆ ወልቃይትን፣ ሁመራና ጠገዴን ከጎንደር ቆርሶ የትግራይ ክልል ያደረገውን የወያኔ ሕገ አራዊት ቀለም በጥብጦ የጻፈ፤ ጎጃም ለሁለት ተከፍሎ ግማሹ ቤንሻንጉል ክልል ተብሎ ሲፈጠር ፊርማውን ያስቀመጠ፣ ወሎን ለሶስት ተከፍሎ ሰሜኑን ክፍል ደቡብ ትግራይ፣ ምስራቁ የአፋር ክልል ተደርጎ ሲካለል አብሮ ያረቀቀ፣ ሸዋ ለአምስት ተከፍሎ ከአምስቱ ክፍልፋይ ወያኔ «ሰሜን ሸዋ» ያለውን አንዱን ስንጣቂ ብቻ ወያኔና ኦነግ የፈጥሩት የዐማራ ክልል እንዲሆን አብሮ የሰራ፤ ዐራና ኦሮሞን ዙሪያውን በማነቅ በሱዳንና በጎንደር-ጎጃም- ወለጋ መካከል እየተዋሰነ ቤንሻንጉል የሚባለውን ክልል ጠቅልሎ ጋምቤላን በማቀፍ ከመረብ እስከ ባሮ የተዘረጋች የታላቋ ትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት የሚያስችለውን የወያኔ ፕሮግራም «በምሁር ስም» ሕጋዊ በማድረግ ረገድ ሽፋን ሆነ ትውልድና ታሪክ ይቅር የማይለው ከሃዲ ነው።

ክፍሌ ወዳጆ ለፋሽስት ወያኔ ለዋለው ለዚህ ሁሉ ውለታው በዘንድሮው አመት የሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ «ሕገ መንግስቱን በማርቀቅ ሂደት ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው» ተብሎ «ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ መብት ላበረከቱት አስተዋፅኦ» የሚል የፋሽስት ወያኔን የክብር እውቅና ሽልማት ተቀብሏል። ፋሽስት ወያኔ እንደ ክፍሌ ወዳጆ አይነት ሆዳም አጋስሶችንና የዐማራ ቀንደኛ ጠላት የሆኑት ነውረኞችን ሲሸልም ክፍሎ ወዳጆ የመጀመሪያው አይደለም።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ባለፈው ሰሞን የመለስ ዜናዊ ነፍስ አባት የሆነው ፖል ሔንዚን ማህደር የማየት እድል አጋጥሞኝ አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶቹን ለማየት ችዬ ነበር። ፖል ሔንዚ በጻፈው ምስጥራዊ ማስታወሻ ላይ እንደሰፈረው እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 1989 አ.ም. ጀምሮ ወያኔ በብርሀነ ገብረ ክርስቶስ አማካኝነት አሜሪካና አውሮፓ አገራት የሚኖሩ ሆዳም ዐማሮችን ለኢሕዴን አባልነት እየደለለ በብዛት እንደመለመለ አስፍሯል። ፋሽስት ወያኔ ለብአዴን አባልነት በብርሀነ ገብረ ክርስቶስ በኩል እ.አ.አ. በ1990 አ.ም. ከአሜሪካን ከመለመላቸው ሆዳም ዐማሮች መካከል የወያኔ አፈ ጉባኤ የነበረው ዳዊ ዮሐንስ ቀዳሚው ነበር። ብርሀነ ገብረ ክርስቶስ ዳዊት ዮሐንስን ለብአዴን አባልነት ከመለመለ በኋላ ለዳዊት የሰጠው የቤት ስራ እንደሱ ያሉ ሆዳም ዐማሮችን ለኢሕዴን አባልነት እንዲመለምል ነበር። ዳዊት ዮሐንስም በተሰጠው የቤት ስራ መሰረት ብዙ ሳይቆይ ዘመዶቹ የሆኑትን እነ ክፍሌ ወዳጆችን፣ ገነት ዘውዴን፣ የምርጫ ቦርድ «ኃላፊ» የነበረውን አሰፋ ብሩን፣ ወዘተን ከያሉበት ለቃቅሞ የኢሕዴን አባላት እንዲሆኑ ለብርሀነ ገብረ ክርስቶስ አስረከባቸው።

ፖል ሔንዚ በጻፈው ማስታወሻ ላይ በግልጽ እንደሰፈረው የነ ዳዊት ዮሐንስና የኢሕዴን ሚና በግልጽ ይታያል። ፖል ሔንዚህ ከብርሀነ ገብረ ክርስቶስ ጋር ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ጽህፈት ቤት ስለ ኢሕአዴ መጻኢ እንድል ለመወያኔት ጉባኤ ሲዘረጉ ከብርሀነ ገብረ ክርስቶስ ጋር የነበረው ዳዊት ዮሐንስ «ሻይ አቅርቦልን በሩን ዘግቶ ከቤት ወጣና እዳሪ ተቀመጠ» ይለዋል። ልብ በሉ። የኢሕአዴግ «መስራች» የሆነው ኢሕዴን «አመራር» አባል የሆነው ዳዊት የሕወሓቱ ብረሃነ ገብረ ክርስቶስ ስለኢሕአዴግ እድል ፈንታ ለመወያየት ከፖል ሔንዚ ጋር ውይይት ለማድረግ ጉባኤ ሲከፍት ሎሌው ዳዊት ግን ሚናው የሆነውን ሻይ ማቅረብ ከውኖ በኢሕአዴግ ስም የሚደረገውን ስብሰባውን ለአለቃው ለብርሀነ ገብረ ክርስቶስ ትቶለት ወጣ። ወያኔ የዐማራ አመራር አድርጎ የፓርላማው አፈ ጉባኤ ሹመትን የሰጠው ዳዊት ዮሐንስ የኢሕአዴግ ጉዳይ ከአማሪካኖች ጋር ውይይት ሲደረግ የሕወሓት ሻይ አቅራቢ ሆኖ ደጅ ይጠብቅ የነበረውን አጋሰስ ነው። ይህ ማለት ወያኔ ዐማራን እየገዛ ያለው ሻይ አቅራቢ ሎሌዎቹን በመሾም ነው ማለት ነው። መቼም ከዚህ በላይ በዐማራ ላይ የሚሰንዘር ንቀት አይኖርም። ወያኔ ኦሮሞን የሚገዛው ሻዕብያ ከደርግ ጋር ጦርነት ሲያካሂድ ለሕዝባዊ ግንባር እጃቸውን በሰጡ ምርኮኞች እንደሆነ መናገር መቼም ለቀባሪው ማርዳት ነው።

እንግዲህ! ብአዴን የሚባለው የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅት እንደ ዳዊት ዮሐንስ አይነት የወያኔ ሻይ አቅራቢ ሆዳሞች የተከማቹበት፤ ሲጠሯቸው አቤት፣ ሲልኳቸው ወዴት የሚሉ የዐማራን ክብር ያዋረዱ አጋሰሶች የተከማቹበት ማህበር ነው ማለት ነው። የነዚህ ነውረኞች ተግባር «ዐማራን በማዳከምና በማጥፋት የትግራይን ሪፑብሊክን መገንባትና ማጠናከር» የሚለውን «የመለስ ራዕይ» እና የሕወሓትን ትውልድ ተሻጋሪ ግብ በዐማራ ሕዝብ አናት ላይ ተሰይመው የትግራይን ጥቅም በዐማራ መቃብር ላይ ያለገደብ ማስፈጸም ነው።

እርግጥ ነው ፋሽስት ወያኔ ከአሜሪካና አውሮፓ የለቃቀማቸውን የወያኔ ሻይ አቅራቢዎች፣ ከኢሕአፓ ኮብልለው ለሕወሓት ያደሩ ወዶ ገብ ፋኖዎችና ሻዕብያ የማረካቸው «የደርግ» ወታደሮች ተሰባስበው በወያኔ አጋፋሪነት የመሰረቱት ድርጅት ኢሕዴን የሚባል የጫካ ስም ነበረው። ይህ የድርጅት መጠሪያ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በአንድ ቀን ሌሊት ብአዴን ወደሚል የዳቦ ስም ተለውጦ ያደረውና በኤርትራዊው በመብርሀቱ ገብረ ሕይወት [በወያኔ ስሙ በረከት ሰምዖን] እና በትግሬዎቹ በነካሳ ተክለ ብርሃን እንዲዘወር የተደረገው የዐማራን ውልክና ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መዐሕድ ለመጫረትና የዐማራ ነስፍ አድን መዐሕድን ለመዋጥ ነበር። ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃም ባይሆን ባመዛኙ ይህን የወያኔ አላማ ከመዐሕድ ውስጥ እንደ ቀኛዝማች ነቃጥበብ በቀለ አይነት ሆዳሞች በመነሳታቸው፤ ከውጭ ደግሞ ፋሽስት ወያኔ የፈጠረው ነውረኛው ብአዴን በጋራ ሆነው ለዐማራ የሚቆረቆረውን ድርጅት [መዐሕድ] በመዋጥ ለወያኔ ማስገበር ባይችሉም ማጥፋት ግን ችለዋል።

Share this post

One thought on “የጎንደር ጉዳይ – (ክፍል ፩)

  1. Achameleh, good remarks. I love your postings. Look where kiflie wodajo is now. He is in hell. He never enjoyed the life he wanted. He did not get the chance to live long. So the hodams are not eternal people.

    Reply

Post Comment