የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “መደመር” መፅሐፍ ምን ይዟል?

Source: https://mereja.com/amharic/v2/159779

BBC Amharic : “ከኢትጵያዊያን መሠረታዊ ሥሪት የሚነሳ፣ ችግሮቻችንን ሊፈታ የሚችል፣ እኛው እያቃናነውና እያሟላነው የምንሄደው፣ ከዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ፣ ሁላችንንም ሊያግባባና ሊያስተሳስር የሚችል አንዳች ሉዓላዊና ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ያስፈልገናል” ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ቅዳሜ በመዲናዋ አዲስ አበባ እና በሌሎችም በርከት ያሉ ከተሞች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ባስመረቁት አዲስ መፅሐፋቸው “መደመር” ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች ደጋግመው ያወሱትና መደመር ሲሉ የሚጠሩትን የአመራር እሳቤያቸውን ጠቅለል ባለ አኳኋን ለመተንተን የሞከሩበት፣ በልዩ ልዩ የመንግስት እንደዚሁም የአኗኗር አፅቆች እሳቤያቸው እንዴት ሊተገበር እንደሚችል ለማመላከት የጣሩበት፣ ከዚህም በዘለለ የአስተዳደራቸውን ቀጣይ አቅጣጫዎች በተመለከተ ፍንጭ የሰጡበት ድርሳን ነው “መደመር”።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "መደመር" መፅሐፍ
በአስራ ስድስት ምዕራፋት የተቀነበበው መደመር የጠቅላይ ሚኒስትሩን ግላዊ ምልከታዎች ጥንስስ እና ዕድገት አስረድቶ አያበቃም፤ ኢትዮጵያ በእርሳቸው አመራር በፖለቲካ፣ በምጣኔ ኃብት እና በውጭ ግንኙነት መስኮች ምን መልክ እንዲኖራት እንደሚሹ የሚጠቁም ሲያልፍም በግላጭ የሚያስቀምጥ ጭምርም ነው።
“ጊዜያችንን የሚዋጅ እሳቤ ነው” የሚሉትን የመደመርን ፅንሰ ኃሳብ በጥቅሉ ሲበይኑት “ከትንተና አንፃር ሀገር በቀል”፣ ከመፍትሔ ፍለጋ አንፃር ደግሞ “ከሀገር ውስጥም ከውጭም ትምህርት በመውሰድ የተቀመረ ነው” ይሉታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመፅሐፋቸው ሙግታቸውን የሚጀምሩት ስለሰው ልጅ ፍላጎቶች ከፍልስፍናም ከሥነ ልቦና ሳይንስ ደጆች የሚታከክ ትንተና በማቅረብ ነው። ሰዎች በህይወቶቻቸው ቀጥተኛ የህልውና ፍላጎቶች፣ የስጋ ፍላጎቶች እንዲሁም የመልካም ስም ወይንም የክብር ፍላጎቶች ሰንገው እንደሚይዟቸው ያስረዱና የመደመር እሳቤ እነዚህን ፍላጎቶች

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.