የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

Source: https://fanabc.com/2018/12/%E1%8B%A8%E1%8C%A3%E1%88%8A%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%89%B5%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8A%A2/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ዲልሪ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው።

ሚኒስትሯ ከነገ ጀምሮ ለአራት ቀናት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ፥ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በቆይታቸውም ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴርና ግብርና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋራ ይወያያሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ የሚገኘውን የጣሊያን የባህል ማዕከልና የደንቦስኮ የወጣቶች ማዕከልና ትምህርት ቤትን እንዲሁም በጣሊያን መንግስት የሚደገፈውን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ተቋምን እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ ከሚኖሩ የጣሊያን ማህበረሰብና በተለያየዩ ዘርፎች በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ ካሉ የጣሊያን ባለሀብቶች ጋርም ይወያያሉ ነው የተባለው።

 

 

Share this post

One thought on “የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.