የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ አዲስ አበባ ገቡ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%8B%A8%E1%8C%A3%E1%88%8A%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8C%88/

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 01፣2011(ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢጣሊያን ማህበረሰብ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ ለክብራቸው መድፍ ተተኮሶላቸዋል።

ጁሴፔ ኮንቴ በዛሬው እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.