የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ዶ/ር አሚር ከስልጣን ተሰናበቱ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/189209

የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚንስትር የነበሩት ዶክተር አሚር አማን ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።
ከወራት በፊት የሥራ መልቀቂያን አስገብተው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)ን ምላሽ ሲጠባበቁ የከረሙት ዶክተር አሚር ጥያቄቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ይፋ አድርገዋል።

በህክምና ሙያ ትምህርት የተመረቁት የቀድሞው ሚንስትር ከ2001 ጀምሮ ወደ ሥራው ዓለም የተቀላቀሉ ሲሆን ለዓመታት በጤና ጥበቃ ሚንስትር ዴኤታነትም አገልግለዋል።
ከሚያዚያ 2010 ጀምሮ ደግሞ የጤና ሚንስትር ሆነው እስከዛሬ ሰርተዋል።
በቀጣይ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዓለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሥራን ሊጀምሩ እንደሚችሉ እየተነገረላቸው የሚገኙት ዶክተር አሚር የኢትዮጵያን ሕዝብ በቻሉት ሁሉ እያለገሉ እንደሚኖሩ ቃል ገብተዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.