የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ም/ቤት ተላለፈ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168448

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 75ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
(ኤፍ ቢ ሲ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 75ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በአገራአችን የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊ አገራዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ ለማደውረግ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የሪፎርም ሥራዎችን ለማከናወን እንዲቻል አዲስ አዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል፡፡ በአዲሱ አዋጅ ከተካተቱ አዳዲስ አደረጃጀትና መዋቅሮች ጋር ለማጣጣም፣ በስራ ላይ ባለው ደንብ የታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን ለማስተካከል፣ የመከላከያ ሰራዊቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማቃለል የሚረዱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን ለማካተት በሚያስችልና የመከላከያ ሰራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸምና ሞራላዊ ዝግጁነት ለማጠናከር ሲባል የመከላከያ ሰራዊት ደንብ ቁጥር 385/2008ን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የመከላከያ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ም/ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማከል ደንቡ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በአሁኑ ወቅት በተግባር ስራዎችን እያከናወነ ያለበት ሁኔታ ከተጣለበት ሃላፊነት እና አላማውን ከመፈጸም አኳያ የደንቡ አንዳንድ ክፍሎች ግልጸኝነትን ባለው መንገድ ያልተመላከቱ ስለሆነ የማቋቋሚያ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የመከላከያ ሚኒስቴር ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ም/ቤቱም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.