የጨው ምርት በአይዮዲን በልጽጎ ደርጃውን በጠበቀ መልኩ ለገበያ እየቀረበ አይደለም

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%A8%E1%8C%A8%E1%8B%8D-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8B%AE%E1%8B%B2%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%8D%E1%8C%BD%E1%8C%8E-%E1%8B%B0%E1%88%AD%E1%8C%83%E1%8B%8D%E1%8A%95/

አዲስ አበባ፣ መስከረም29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ መድሃኒት፣ ጤና  ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ፥የጨው ምርት በአይዮዲን በልጽጎ እና ደርጃውን በጠበቀ መልኩ ተዘጋጅቶ  ለተጠቃሚዎች እየቀርበ እንዳልሆነ አስታውቋል ።

አስገዳጅ ህጉ ቢውጣም ተግባራዊ እየተደርገ አይደለም ያለው ባለስለጣኑ ፥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ከምርት እስከ ተጠቃሚው ድርስ በአሰራር ሂደት ጨው የአይውዲን ይዘቱን እንደሚቀንስ እና ለከፋ የጤና ችግር እንደሚዳርግም  የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ሲስተር ህይወት ገሚካኤል ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ከ500 በላይ ጨው አምራች ማህበራት የሚገኙ ሲሆን፥  ከእነዚህ ውስጥ ጥራት እና ደርጃውን ጠብቀው የሚያመርቱት  ከሁለት የማይበልጡ  ፋብሪካዎች  ብቻ መሆናቸው  ተመላክቷል።

በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጨው ምርት በአይዮዲን በልጽጎ እንዲቀርብ የግንዛቤ  ማስጨበጫ  ስራ እንደሚስራም ተገልጿል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.