የፌዴራል ሥርዓቱም ወደ ኣሃዳዊነት እየሄደ መሆኑን ተረድቼያለሁ – የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሀመድ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/178377

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።
DW : የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሀመድ በጀርመኗ ኑርንበርግ ከተማ ከደጋፊዎቹ ጋር በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከመወያየቱ አስቀድሞ ዶቼቬለ በኑርንበርግ ቃለ መጠይቅ አድርጎለት ነበር።
 Äthiopien Addis Abeba Oppositionsführer Jawar Mohammed (picture-alliance/AP Photo/M. Ayene)

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሀመድ በጀርመኗ ኑርንበርግ ከተማ ከደጋፊዎቹ ጋር በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከመወያየቱ አስቀድሞ ዶቼቬለ በኑርንበርግ ቃለ መጠይቅ አድርጎለት ነበር።ጀዋር በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ በግንቦት ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቅባት በኢትዮጵያ ከመንግስትም ሆነ ከተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች በኩል እስካሁን በቂ የሚባል እንቅስቃሴ እየታየ አይደለም ሲል ወቀሷል።የፌዴራል ሥርዓቱም ወደ ኣሃዳዊነት እየሄደ መሆኑን ተረድቼያለሁ የሚለው ጃዋር ይህንኑ ለመታደግ ከወዲሁ አጀንዳ አድርጎ ስለመነሳቱም አብራርቷል።ጉዳዩ ዋነኛ የምርጫ መከራከሪያው እንደሚሆንም  ጀዋር ለዶይቸ ቬለ ገልጿል።
Protest gegen Jawar Mohammed in Nürnberg (B. Belay )
ጀዋር መሐመድ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት በሚያደርገው በዚሁ የቅስቀሳ ጉዞው በደጋፊዎቹ ከሚደረግለት አቀባበል ጎን ለጎን ተቃውሞም ገጥሞታል። በደረሰባቸው ስፍራዎች ተቃዋሚዎቹ በቅርቡ በኢትዮጵያ ከ80 ሰዎች በላይ ህይወትን ለቀጠፈው ደም አፋሳሹ ግጭት ተጠያቂው ጀዋር እንደሆነ ሲናገሩ ተሰምቷል። በኑርንበርግ ከተማም ተመሳሳይ የተቃውሞ ተሰምቷል። ጀዋር ስለዚሁ ጉዳይ ዶቼቬለ ላነሳለት ጥያቄ በሰጠው መልስ፣ «ተጠያቂ መሆን ያለበት ችግሩን የፈጠረው መንግስት ነው» ሲል ተናግሯል።
በተለያዩ መድረኮች የኢህአዴግን መዋሃድ ሲነቅፍ የሚሰማው ጀዋር በፓርቲው የውስጥ ጉዳይ ላይ ለምን ተቃውሞህን አሰማህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ኢህአዴግ የብልጽግና ፓርቲ ሆኖ የመዋሃዱን ነገር እንደ ጀዋር ሁሉ የቀድሞው የኢህአዴግ አባል ድርጅት የነበረው ህወሃትም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.