የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ውስጥ አደገኛ መርዝ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/79491

ታምሩ ጽጌ

የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪዎች ተቋማትም ተጠያቂ መሆን አለባቸው አሉ
የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ውስጥ አደገኛ መርዝ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የመርዙን ዓይነትና የጉዳት መጠን በባለሙያ ለማስመርመር እየሠራ መሆኑን በመግለጽ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገውም ገልጿል፡፡
መርማሪ ቡድኑን በመቃወም ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ቤቱ በተቋሙ ውስጥ መርዝ እንዳለ የተናገሩት እነሱ መሆናቸውን አስረድተው፣ ይኼንንም ያደረጉት መርዙ አደገኛ በመሆኑ ዜጎች ሳያውቁ ቢነኩት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል በማለት አስበው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን መርማሪ ቡድኑ ራሱ በምርመራ እንዳገኘው አድርጎ ለፍርድ ቤቱ በማቅረብና በማስረዳት፣ የተጨማሪ ጊዜ መጠየቂያ ማድረጉ ተገቢ አለመሆኑንና ፍርድ ቤቱ ሊቀበለው እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በማጣሪያ ጥያቄ መርማሪ ቡድኑ መርዙን ያገኘው የፍርድ ቤት መበርበሪያ ትዕዛዝ ወስዶ ባደረገው ብርበራ መሆን አለመሆኑን ሲጠይቀው፣ ‹‹በተጠርጣሪዎቹ ጥቆማ ነው፤›› ብሏል፡፡
በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች፣ እነሱ በወንጀል ከተጠረጠሩ ይሠሩባቸው የነበሩ ተቋማትም ስለሚመለከት፣ እነሱም መጠየቅ እንዳለባቸው ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡
በአቶ ጐሃ አጽብሃ የምርመራ መዝገብ የተካተቱ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አባላት የነበሩ 33 ተጠርጣሪዎች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት እንዳስረዱት፣ ተጠርጥራችኋል የተባሉት ሕጋዊ ሆነው ሲሠሩባቸው በነበሩበት ተቋማት ውስጥ በመሆኑ፣ ተቋማቱም ሊጠየቁ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ብቻቸውን ተጠያቂ ሊሆኑ እንደማይገባ ለፍርድ ቤቱ የገለጹት፣ የተጠረጠሩበትን የወንጀል ድርጊት በማጣራት ላይ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.