የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77395

ENA – የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመከላከል የሚያስችል ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ።

ምክር ቤቱ በማንነት ጉዳዮችና የጥያቄዎች አፈታት ላይ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ነው።
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንደገለጹት፤ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥ ውስንነት ነበረው።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በማንነት ጥያቄዎች ላይ የማይመለከታቸው አካላት እጃቸውን በማስገባት ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
”ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 62 በተሰጠን ስልጣን መሰረት ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት እስካሁን 76 ብሔሮች ዕውቅና ያገኙ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ኬርያ በቀጣይ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ እንደሚያገኝ አረጋግጠዋል።

Share this post

One thought on “የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.