የፓናማ ፖሊስ 79 እሽግ ፖኮ አደገኛ እጽ አንድ ባለስልጣን ሲያዘዋውሮ መያዙን ተናግሯል፡፡

የአገሬው ሚዲያ ይህንን ያህል እሽግ እጽ በመኪናቸው ደብቀው ሲሄዱ

ከተያዙት መካከል አንድ ባለሥልጣን እንዳሉበት ገልጸዋል፡፡

የጉና ያላ ግዛት ገዥ የሆነት ኤሪክ ማርቴሎ ናቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት ድንገት አሰሳ ማድረጉን ተናግሯል፡፡ አሰሳውን ያደረገው ዋና መንገድ በመዝጋትና መኪናዎችን በመበርበር ነበር፡፡

አደገኛ እጾቹ የተገኙት በመኪናው መቀመጫዎች ሥር ተወትፈውና ተጠቅጥቀው ነው፡፡

የፓናማ ፕሬዝዳንት ኒቶ ኮርቲዞ በትዊተር ገጻቸው እኛ የሕዝብ አገልጋዮች ነን፤ ማንኛውንም ከመስመር የወጣ ባለሥልጣን አንታገስም ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply