የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ አጀንዳዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8B%A8%E1%8D%96%E1%88%88%E1%89%B2%E1%8A%AB-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%89%80%E1%8C%A3%E1%8B%AD-%E1%8A%A0%E1%8C%80%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%8B%8E%E1%89%BB%E1%89%B8/

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ አጀንዳዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው፡፡

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ በሚወያዩባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ቀደም ሲል ሃሳባቸውን ለምርጫ ቦርድ ማቅረባቸው ይታወሳል።

እነዚህን የሃሳብ ነጥቦች ወደ 7 በማጠቃለል በጉዳዮቹ የቅደም ተከተል ላይ በዛሬው እለት ከምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ ይገኛል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምርጫ ቦርድ ጉዳይ እንዲሁም ምርጫ 2012 እና የአካባቢ ምርጫ፥ በፖለቲካ ፓርቲዎቹ በመጀመሪያ ደረጃ ቀርቧል።

ከዚህ ባለፈም የህገ መንግስትና ፌደራል ጉዳዮች እንዲሁም የህገ መንግስትና ፌደራሊዝም ጉዳዮችም በፓርቲዎቹ ቀርበዋል።

በእነዚህ ነጥቦች ቅደም ተከተል ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተለያዩ ሀሳቦቻቸውን አንስተው፥ በጉዳዮቹ ቅደም ተከተል ላይ እየመከሩ ነው።

ዶክተር ጥላዬ ካሳሁን፣ ዶክተር ሽፈራው ሙለታ፣ ዶክተር ሰሚር የሱፍ፣ አቶ ሄኖክ አክሊሉና አቶ አምሃ መኮንን በቀጣይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን ውይይት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በእነዚህ አጀንዳዎች ዙሪያም በዛሬው እለት ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ ፈርመው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መድረሳቸው የሚታወስ ነው።

በፋሲካው ታደሰ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.