የ10ኛ ክፍል ፈተና ከሃገሪቱ የትምሕርት መዋቅር ላይ ተሰረዘ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139712

EBC : የአዲሱ የትምህርት መዋቅር (6-2-4) በሚል ማሻሻያ ተደረገ – የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናዎች ከ12ኛ ክፍል በኋላ እንደሚጀምር ተገለጸ
አዲሱ የትምህርት መዋቅር 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ18 ዓመት የሚያጠናቅቁ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ ገልጸዋል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በግል ዘርፍ ተይዞ የቆየው የቅድመ መደበኛ ትምህርት በግልና በመንግስት እንዲያዝ መደረጉም ተጠቅሷል፡፡
ተማሪዎች 6ኛ ክፍል ሲያጠናቅቁ ክልላዊ ፈተናን እንደሚፈተኑና ከዚህ በፊት ክልላዊ ፈተና የነበረው 8ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡በዚህም የ10ኛ ክፍል ፈተና እንደማይኖርና የ12ኛ ክፍል ፈተናው ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቲቪቲ ሁሉም ስልጠናዎች ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርሃ ግብር ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 8 ወይም እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ድረስ መማር እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል መምህራን ባላቸው የትምህርት ደረጃ ላይ መሰረት በማድረግ የመምህራን ድልድል መሰራቱም ተገልጿል፡፡በዚህም የአንደኛ ደረጃ ከመምህራን የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፣ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው እንደሚመደቡ ተገልጿል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.