የ17 የምግብ ዘይት ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ መጠቀም እንደሌለበት ተገለጸ

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%8B%A817-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%8C%8D%E1%89%A5-%E1%8B%98%E1%8B%AD%E1%89%B5-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8A%90%E1%89%B6%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%88%85%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B0/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የ17 የምግብ ዘይት ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ መጠቀም እንደሌለበት አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ባደረገው የገበያ ጥናት ነው 17 የምግብ ዘይት ምርቶች ላይ መሰረታዊ ችግር እንዳለባቸው ያስታወቀው፡፡

ምርቶቹ የሚመረቱበት ቦታና የተመረተበት ሀገር፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የአምራች አድራሻ፣ የገላጭ ጽሁፍ ችግር ያለባቸው ናቸው ብሏል፡፡

የመጠቀሚያ ጊዜና ማብቂያ ቀን የሌላቸው እና የሀገሪቱን የደረጃ ምልክት ያለጠፉና ደረጃውንም የማያሟሉ እንደሆነም ይፋ አድርጓል፡፡

ምርቶቹም ሉሉ ዘይት፣ አርሲ ዘይትአሃዱ ዘይት፣ ድሬ ንጹህ የምግብ ዘይት፣ አሚን ንጹህ የምግብ ዘይት፣ ሮያል የምግብ ዘይት፣ ዳግም የተጣራ የኑግ ዘይት፣ ጄጃን የምግብ ዘይት፣ ውብ የተጣራ የኑግ ዘይት፣ ለማ የኑግ ዘይት፣ ኑድ ንጹህ የምግብ ዘይት፣ ገበታ የምግብ ዘይት፣ ዘመን ዘይት አጋር ዘይት፣ አናጅና ዘይት፣ ሳባ ዘይት እና ጃሎ ዘይት መሆናቸውን ነው ያስታወቀው

ህብረተሰቡ ምቶችን ሲገዛ የተመረቱበትና የመጠቀሚያ የአገልግሎት ጊዜው ትክክለኛነት፣ ያልተፋቀና ያልተሰረዘ መሆኑን እንዲያረጋግጥም አሳስቧል፡፡

የአምራች ድረጀቱ ስምና ሙሉ አድረሻ፣ የምርት መለያ ቁጥር ያለው የምርት ገላጭ ጹሁፍችን ያላሟላ ምርቶችን መጠቀም እንደሌለበት ነው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡

ተመሳሳይ ችግሮች ሲያጋጥሙም ለፖሊስ ወይም ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 መረጃ እንዲሰጥም መልክቱን አስተላልፏል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.