የ40/60 የጋራ ቤቶችን ሊዘርፉ በነበሩ ግለሰቦች ጥቃት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ ሕይወታቸው አለፈ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/181620

የ40/60 የጋራ ቤቶችን ሊዘርፉ በነበሩ ግለሰቦች ጥቃት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ ሕይወታቸው አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የከተማ አስተዳደሩ የቁጠባ ቤቶች ግንባታ ልማት ኢንተርፕራይዝ እያስገነባቸው ያሉ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሊዘርፉ በነበሩ ግለሰቦች ጥቃት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ይዞ በምርመራ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ረቡዕ ታኅሳስ 1 ሌሊት ቁጥራቸው 30 የሚሆኑ ግለሰቦች ተሽከርካሪ ይዘው ረድኤት ዳግም ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከኢንተርፕራይዙ ኮንትራት ወስዶ እየገነባው ባለው 160 አባወራዎችን በሚይዘውና ባለ 15 ፎቅ በሆነው ሁለት ብሎክ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመዝረፍ መምጣታቸውን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳግማዊ ፋሲል ገልጸዋል፡፡

በውድቅት ሌሊት ለዝርፊያ የመጡት ግለሰቦች በዕለቱ በጥበቃ ላይ በነበሩት አቶ ሹመት ተገኝ የተባሉ የማኅበሩ ሠራተኛ ላይ ከባድ የድብደባ ጥቃት አድርሰውባቸው ለሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም፣ ሐሙስ ታኅሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል፡፡
Via The Reporter Newspaper

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.