ዩኒቨርሲቲዎቻችን ከችግር ፈችነት ይልቅ የችግር መፈልፈያ በመሆን ላይ ናቸው – የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/185562

‹ዩኒቨርሲቲዎቻችን ከችግር ፈችነት ይልቅ የችግር መፈልፈያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡›› የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ማስፈንን ዓላማው ያደረገ ውይይት ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ከከተማው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡
ለረጅም ጊዜያት በሠላማዊነቱ የሚታወቀውና ሠላምን መለያው ያደረገው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም ከድህረ ምረቃ ትምህርቶች ውጭ ባሉ ኮሌጆች ካለፈው ኅዳር ወር ጀምሮ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሲቆራረጥ ቆይቷል፡፡

ሠላም ሠፍኖ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል ለማድረግም ከተማሪዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፤ ዛሬም ከከተማዋ ነዋሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋርም ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በውይይቱ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ችግር እስከተፈጠረበት የነበረውን ውጣውረድ የዳሰሰ የውይይት መነሻ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን በተለይም ዩኒቨርሲቲው በሠላማዊ ሁኔታ ላይ በነበረበት ጊዜ ‹‹ኃላፊነት የጎደላቸው መገናኛ ብዙኃን የሚያቀርቧቸው የተዛቡ መረጃዎች አለመረጋጋት እንዲሰፍን እና የሕይወትና ንብረት ጉዳቶች እንዲደርሱ መነሻ ሆኗል›› ብለዋል:: ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ሂደቱ እንዲቀጥል ጥረት ቢያደርግም በአማርኛና ኦሮሞኛ ቋንቋዎች በራሪ ጽሑፎች መበተናቸውና ተማሪዎች እንዳይረጋጉ ማድረጉ በርካታ ተማሪዎች በስጋት ግቢውን ለቅቀው እንደወጡ አመልክተዋል፡፡
በችግር ፈጣሪነት የተጠረጠሩ ተማሪዎች የአስተዳደር ሠራተኞችና አንድ መምህር በምርመራ ላይ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡
የአብክመ ሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር ደግሞ ‹‹በሌላ ክልል የሚኖሩ ተማሪዎቻችን በሠላም እንዲኖሩ በክልላችን የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ ሠላም ማስፈን ይገባናል›› ብለዋል አቶ አገኘሁ፡፡
በዚህ ዓመት ብቻ ከአማራ ክልል ወደ ዩኒቨርሲቲ የተቀላቀሉ ተማሪዎች

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.