ዩኒቨርሲቲዎችን የሚጠብቁ ፖሊሶች ድልደላ እያካሄደ መሆኑን ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/183085

ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚጠብቁ ፖሊሶች ድልደላ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ አዳዲስ ተመራቂ የፖሊስ አባላትን ዩኒቨርሲቲዎች ላይ በቋሚነት የመመደቡ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብሎናል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጄይላን አብዲ እንደነገሩን፣ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አዳዲስ ምሩቅ ፖሊሶች ሀገሪቷ ካለችበት ቀውስ ጋር ተያይዞ፣ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ሁሉንም ህብረተሰብ በቅንነት ያለ አድሎ እንዴት ማገልገል እለባቸው በሚለው ላይ ስልጠና መውሰዳቸውን ነግረውናል፡፡
ከተማራቂዎቹም መካከል የተወሰኑት በቋሚነት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚገቡ እና ፀጥታ የማስከበር ስራቸውን እንደሚጀምሩ አቶ ጀይላን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ተፈጥረው በነበሩ ችግሮች ምክንያት ከዚሀ ቀደም የነበሩ ፌደራል ፖሊሶዎች፣ መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች አዲስ ከሚመደቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ተቀናጅተው የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም ለመጠበቅ ይሰራሉም ብለውናል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚመደቡት የፀጥታ ሀይሎች ቁጥር አለመታወቁን የነገሩን ዳይሬክተሩ፣እንደ ዩኒቨርሲተዎቹ ፍላጎት እና የፀጥታ ሁኔታ ቁጥራቸው እንደሚለያይ ነግረውናል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.