ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት በፍጥነት እንደሚገቡ ተገለፀ

ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት በፍጥነት እንደሚገቡ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት ዓላማ በፍጥነት መግባት እንዳለባቸው ተጠቆመ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዩኒቨርሲቲዎቹን በትኩረት መስክ መለየት የሀገሪቱን ብልጽግና ለማሳካት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ዓርአያ ሆነው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚፈልገውን ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲዎች ልየታ ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎቹን ለማበላለጥ ሳይሆን ከነበራቸው የትኩረት አቅጣጫ በመነሳት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡
በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት ውጤት መሠረት 8 የምርምር፣ 15 የአፕላይድ ሳይንስ፣ 2 የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ቀሪዎቹ 21ዱ የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ተብለው መለየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

The post ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት በፍጥነት እንደሚገቡ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply