ያሬድ ጥበቡ የበረከት ስምዖን መልቀቅን በበጎ ጎኑ አላየሁትም አሉ | “በረከት መለስ ከሞቱ በኋላ በድርጅቱ ሥራ እርካታ እንደማይሰማቸው ይታይ ነበር” – ቻላቸው ታደሰ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81718

(የጀርመን ድምጽ ራድዮ ዘገባ እንደወረደ) አንጋፋዉ የኢሕአዴግ ታጋይና ባለሥልጣን አቶ በረከት ስምዖን ኃላፊነታቸውን “ለመልቀቅ” ደብዳቤ ማስገባታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አረጋግጧል። በመንግሥትና በገዢው ግንባር ውስጥ “አድራጊ ፈጣሪ፤ ሿሚ ሻሪ” ናቸው የሚባልላቸው አቶ በረከት ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ከቆዩበት የሥልጣን አካባቢ መራቅ የፈለጉበት ምክንያት እስካሁን በይፋ አልተገለጠም። በሚንስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ […]

Share this post

One thought on “ያሬድ ጥበቡ የበረከት ስምዖን መልቀቅን በበጎ ጎኑ አላየሁትም አሉ | “በረከት መለስ ከሞቱ በኋላ በድርጅቱ ሥራ እርካታ እንደማይሰማቸው ይታይ ነበር” – ቻላቸው ታደሰ

 1. …አቶ ያሬድ ጥበቡ ምንስ ቢሆን በኢትዮጵያ ቀበራ ላይ ከስብሃቱ ገ/እግ ጋር አብረው ጉድጓድ ቆፍረው የለም!?
  ከዚህ በፊትም ብአዴንን አትንኩ ቢያንስ አዲሱ ለገሠን ተከትሉ ሲሉ ነበር…ሕዝቡ በራሱ ሰንደቁን ይዞ ህወሓት/ኢህአዴግን ለሰሞነኛም ቢሆን…ፈጣን/ችኩል አዋጅ አስገደደው። አሁንም ማስደገሙ ወይም በግላጭ ወታደራዊ መንግስት ማሳወጁ አይቀሬ ነው። በመንደር ጥቅማጥቅም ሀገር መንጠቅ የት ያደርሳል? እንዲህ የተከበሩትን ይቀበራል እንጂ….
  __________________!
  “ኢሕአዴግ በፖለቲካዊ ተቃውሞ በሚናጥበት ባሁኑ ወቅት አንጋፋዉ ፖለቲከኛ ሥልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸዉን አቶ ያሬድ በበጎ አይን አላዩትም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሩቅ ሆነው የሚታዘቡት አቶ ያሬድ አቶ በረከት በኢሕአዴግ ውስጥ ያለውን የኃይል ሚዛን ቢያመጣጥኑ የተሻለ ነበር የሚል እምነት አላቸው።” አቶ በረከት ከፖለቲካዊ ተሳትፏቸው ሙሉ በሙሉ ገለል ይበሉ አሊያም በብአዴን አባልነታቸው ይቀጥሉ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።(የህወሓት/ሻቢያ ግርፈኞች አይር(ለ)ቁም!) “ሁላችንም ወያናይት ነን!” ያለው ማን ነበር?
  **************!
  __ይህ ጭብጫቦ የበዛበት ቦለጢቃ አንድ ገፅ ተኩል ሥልጣን ያስጠቀለላቸውን ተጠቅላይ ሚ/ር የጫካው ማኒፌስቶ የከተማው ሕገመንግስት የሚያዳንቅ ተቃዋሚ/ተቋቋሚ ሁሉ የሚያደርጉትን ያውቃሉና ዝም አትበሏቸው!።
  ” አሁን ባላቸው ልምድ፡ ባበረከቱት ዕውቀት፡ባተረፉት ዕውቅናና ተሰሚነታቸውን ታሳቢ በማድረግ የውጭውን ተቃዋሚ በበሳል ፖለቲካ ለማነጽና ሕዝባዊነታቸውን ለማሳየት ሲባል…አቶ በረከት ስምዖን…ኤርሚያስ ለገሠ..ሀብታሙ አያሌውና..ተስፋዬ ግብረእባብ..ያሬድ ጥበቡ…ፓስተር ታምራት ላይናችን በኢሳት ጠረጴዛ ዙሪያ ቢደረደሩስ? ቀስ ብሎ አቶ በረከት ስምዖን ተፀጽተው ያስቀየሙትን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀው ለመካስ ሲሉ የኢሳት የቦርድ ሊቀመንበር ሆኑ ቢባልስ!?
  ተውት መቼም የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ይሉ የለ….!?በለው!።

  Reply

Post Comment