ያሳስባል እንጂ ምነው አያሳስብ ወዳጄ? – ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

እውነቱን ለመናገር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን በአሁኑ ወቅት ብዙ፣ በጣም ብዙ የሚወዘውዟቸውና አብዝተው የሚያስጨንቋቸው ሀገራዊ ጉዳዮች እንዳሉ ጨርሶ ሊስተባበል አይችልም፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፍጻሜና የውሃው ሙሊት፤ ይህንኑ ተከትሎ የተደቀነባቸው የውጭ ሀይሎች ተጽእኖና የውስጥ መሰሪ ባንዳዎቻቸው የሽብር እንቅስቃሴ፤ መያዣ መጨበጫው የጠፋበት የኦሮሞ ጽንፈኞች ፖለቲካ፤ ድህረ-ሲዳማ ሪፈረንደም ትኩሳቱ እየናረ የመጣው የደቡብ ክልል አደረጃጀት፤ የብሔር ፖለቲካው ጡዘት እዚህም እዚያም እያደረሰ ያለው የህዝብ ለህዝብ ግጭትና ከኖረበት ቀየ መፈናቀልና ለተለያዩ ሰብአዊ ችግሮች መጋለጥ፤ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት እያሽቆለቆለ የመጣው ኢኮኖሚና እርሱ በተራው የፈጠረው ማሕበራዊ ምስቅልቅል፤ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ መዳከምና በተለይም ወደብ-አልባነቷን በመንተራስ ሠላምና ደህንነቷን ለመፈታተን ከሁሉም መአዘናት በቀጥታም ሆነ በእጃዙር የሚቀነባበረው ሴራና የሚካሄደው ዘመቻ… ከብዙዎቹ ማሳያዎች መካከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply