ይታየኛል ( ዘ-ጌርሣም)

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107198

ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር ስሜቴ ተውገርገር ድምፅህን አሰማ ህልምህን ተናገር ቅዠትክንም ደርድር ምኞትክን አስረግጥ አድማጭ ድንገት ካለ በአዕምሮው ያመነ የተደላደለ ከአጥናፍ እስከ አጥናፉ ሰላም ሰፍኖ በአገር ፖለቲካው ሰክኖ በውል ሲነጋገር ከጥፋት ዓለሙ ሁሉም ፊቱን ሲያዞር መተሳሰብ ሲነግሥ ልዩነት ሲወንስ ጠላትን ሲከፋው ወዳጅ ደስ ሲለው ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር መለያየት ቀርቶ አንድነት ጎልብቶ በጋራ በመቆም ወገንን ለመጥቀም ሀገርን አልምተን ከልመና ወጥተን ዴሞክራሲ ሰፍኖ ጀብደኝነት በንኖ አንድነት ጠንክሮ ሁሉም ጠግቦ ሲያድር ተርፎትም ሲያካፍል ገበሬው አልፎለት ወጥቶ ከድህነት ተሜ ሲመራመር አዲስ ግኝት ሲፈጥር ይታየኛል ያ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር ማስተዋል ከቻለ የዕይታው መነፅር መጠፋፋት

The post ይታየኛል ( ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.