ይድረስ፡- የአማራ ሕዝብ የኦሮሞኛ ቋንቋ ይማራ እያላችሁ ደብዳቤ ለምትጽፉ ሁሉ – ከቋንቋው በፊት ስለሰው ልጅ ነጻነት እንጩህ!!

Source: http://welkait.com/?p=12961
Print Friendly, PDF & Email

(አያሌው መንበር)

#ከቋንቋው በፊት #ስለሰው ልጅ እንጩህ!!

((ለእነ ፕሮፋሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ አቶ ያሬድ ጥበቡ፣ ግርማ ወልደጊዮርጊስ፣ … ወዘተ)፤ እንዲሁም ደብዳቤው በቀጥታ ለተፃፈለት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፦

Young Tigrayan Cadet Pilots

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ስለሚኖሩ አማራዎች እንግልትና ስቃይ “ጆሮ ዳባ ልበስ” ብሎ፤ በአማራ ህዝብ ላይ ኦሮምኛ ቋንቋን ለመጫን ፊርማ ማሰባሰብ ከስህተትም በላይ ነው፤ ቋንቋውን ጠይቃችሁን ሳይሆን ፈልገነው ነገ እንማረዋለን፤ ዛሬ ግን ስለህመመችን መጮህ ካልቻላችሁ ለቀቅ አድርጉን!!!

በዚህ ሰሞን አስተያየት መስጠት እየፈለግኩ በአንድ በኩል ከጊዜ እጥረት በሌላ በኩል ደግሞ አጀንዳዎች ከመብዛታቸው ጋር ተያይዞ ያለፍኳቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ሆኖም በምናከብራቸው ሰዎች ተፈርሞ ለጥያቄ ወደ አማራ ክልል የተላከው “የኦሮምኛ ቋንቋን በአማራ ክልል ስለማስተማር” የሚጠይቅን #የፖሊሲ ጥያቄ ግን ዝም ብሎ ማለፉ ትክክል ባለመሆኑ የአቅሜን መመለስ ፈልጊያለው።ጉዳዩም የአማራን ህዝብ መብት የሚጋፋ ጉዳይ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

((አንባቢያን እንዲረዱልኝ የምፈልገው ከሀሳብ አመንጮቹ ጋር የግል ቅራኔም ይሁን ጥላቻ የለኝም። ሀሳቡንም ለመሞገት እና ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት እንጅ ለማንቋሸሽ አይደለም።ባለ ብዙ ቋንቋ ባለቤት መሆንንም አበረታታለው))

እነ ፕሬፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “ኦሮምኛ ቋንቋ በግዕዝ አማራ ክልል ላይ” ይተገበር ዘንድ በደብዳቤ ጠይቀዋል።በመጀመሪያ በርቀት ሆኖ ከመሳደብ ይልቅ ምሁራን የድርሻቸውን ለመወጣት እንደዚህ አይነት ተግባር ላይ ሲሰማሩ ሊመሰገኑ ይገባል። ሆኖም የፅሁፉ ጭብጥ ላይ ብዥታ ባይፈጥርብኝም የፅሁፉ አላማ፣ ግብና መነሻ ላይ ግን ተቃውሞየ የጠነከረ፤ ደብዳቤቸውም ውድቅ እንዲሆን የሚያመላክት ነው።

እናም ለጠያቂዎቹ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቸ እንደ አንድ የጉዳዩ ባለቤት ወጣት ልሞግታቸው ወደድኩ። እነዚህን ከታች ያሰፈርኳቸውንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ ምናልባትም ሁላችንም የጠያቂዎቹ መነሻ ስህተትና አላስፈላጊ ወይም ወቅቱን ያላገናዘብ መሆኑን እንደመድማለን።

1. ኦሮምኛ ቋንቋን በአማራ ክልል ለማስተማር ለምን አስፈለገ?ለዚያውም በግዕዝ?

የአማራ ህዝብ ተቻችሎ የሚኖር ማንኛውንም ጎሳ አክብሮ የተቀበለ ህዝብ መሆኑ ልብ ይሏል። በቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ብሄርን መሰረት ያደረጉ መፈናቀሎች ሲከሰቱ በአንፃሩ በአማራ ክልል ግን እስካሁን በውስጡ የሌላ ጎሳ ላይ ጥቃት ተፈፅሞበት የማያውቅ፣ የሌላን ጎሳ መብትም ያልገፋ ነው። የቋንቋም ይሁን የባህል ብዝሀነት ችግር የሌለበት፣ቋንቋ ባለመማሬ ተጎድቻለው ብሎ ሌላ ቋንቋ ለመማር ጥያቄ ያላቀረበ ህዝብ ነው። ታድያ የዚህ ጥያቄ intention/motive ምንድን ነው?

2. አሁን ሀገራችን የገጠማት ችግር የቋንቋ ነው ወይስ የስርዓት? እኔ እስከሚገባኝ የስርዓቱ ችግር ቋንቋን አይደለም ነፍስን እየነጠቀ ነው።

3. ኦሮምኛ ቋንቋን በአማራ ክልል እንዲስያተምሩ ከመጠየቃቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል በየጊዜው ስለሚፈናቀሉ፣ ውክልና ስለተነፈጉ፣ ባህል ወግና ማንነታቸውን ተነፍገው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ስላልተፈቀደላቸው አማራዎች ለምን ፊርማ ማሰባሰብ እና ኦሮሚያ ክልልን መጠየቅ ተሳናቸው? ይህ ጥያቄ የጠያቂዎችን ከጀርባ የረጀም ጊዜ ፍላጎት ይዘው የመጡ ይመስላሉ የሚል ግምት ላይ እንድናርፍስ አያስገድደንም? ከቋንቋ ሳይንሳዊ ውልደትና እድገት ጋርስ አይጣረስም?

4. ኦሮምኛ ቋንቋ መማር አለብን የሚል ፍላጎት ከየትኛው የአማራ ግዛት ነው የመጣው? ለጥያቄው መነሻ የሚሆን ምን ምክንትያ አለ?

5. ቋንቋው መሰጠት ያለበት ለመላው አማራ ወይስ አማራ ክልል ውስጥ ለሚኖሩ ኦሮሞዎች? ለምንስ በግዕዝ?

6. አማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ኦሮሞዎች “በኦሮሚያ ልዩ ዞን” ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ፣ በቋንቋቸው እየተማሩ፣ ባህላቸውን እያበለፀጉ ባሉበት እና ምንም አይነት የአስተዳደር ቅሬታ በማያነሱበት ወቅት አማራ ክልል ላይ ኦሮምኛን ለማስተማር ጥያቄ እንዲነሳ የተፈለገበት ምክንያት የተደበቀ ፖለቲካዊ ፍላጎት ወይስ ዝም ብሎ ቋንቋን ማሳደግ ሌላ?

7. የኦሮምኛ ቋንቋ በኦሮሚያ ክልል ቁቤ በሚባል እየተሰጠ ባለበት በአሁኑ ወቅት አማራ ክልል ላይ በግዕዝ ይሰጥ ማለት ግዕዝን ለማሳደግ ወይስ ኦሮምኛን ለማሳደግ? ወይስ የኦሮሚያ ክልል የሚሰጥበትን ቁቤ ለመቃወምና ቅሬታ ለመፍጠር?

8. ኦሮምኛ በአማራ ክልል በግዕዝ ይስጥ ብሎ ከመጠየቅ በፊት በኦሮሚያ ክልል በቁቤ የሚሰጠው ኦሮምኛ በግዕዝ እንዲቀየር የኦሮሚያ ክልል እንዲተገብረው ማደረግ መቅደቀምስ አልነበረትበም? የቋንቋው የመጀመሪውያ ባለቤት የኦሮሞ ህዝብ ያላደረገውን ሌላውን መጠየቅ ጤነኛ ጥያቄስ ነውን?

9.ኦሮምኛ ቋንቋ መማር የማይፈልገውን ወይም ያልጠየቀውን ህዝብ እኔ አውቅልሃለው መማር አለብህ ብሎ መብቱን መጋፋትስ የአማራን ህዝብ መናቅ ወይም እንደ የዋህ መቁጠር አይደለምን?

10. የዚህ ጥያቄ ዓላማ በኦሮምኛ ቋንቋ ስም አንድነትን፣ መተባበርም፣ መግባባትን በጥቅሉ ኢትዮጵያዊነትን ማስፋፋት /መገንባት ከሆነስ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደርን የአማራ ህዝብ ቤተ ሙከራ ለማደረግ ለምን አስፈለገ?ራሱ ኦሮሞውን ወይም ሌላውን ክልል ቤተሙከራ ማደረግ ለምን አልተቻለም?

11.ከላይ ያለው ዓላማ ኢትዮጵያዊነትን ማጠንከር ከሆነ ለዚህ ሲባል ወደ ባህር ዳር የተደረገን ጉዞ ለምንስ ናዝሬት ወይም ደብረዘይት ወይም ወለጋ ላይ አልተደረገም? እኛ የኢትዮጵያዊነት ችግር ስላለብን ነው ወይ? የሚል ጠንከር ያለ ህዝባዊ ጥያቄ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅትስ በድጋሚ ይህንን አጀንዳ ማምጣት የአማራና ኦሮሞን ህዝብ አብሮነት አያሻክርምን?እንዴት ቢገምቱን ነው? የሚል ጥቄቃ አያስነስምን?

12.የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ ስለሚኖሩ አማራዎች ደህንነትም ይሁን የወደፊት ኑሮ ዋስትና ምንም አይነት ፍንጭ ባልሰጠበት እና አሁንም ጥቃቶች አልፌ አልፎ በሚታዩበት ወቅት የአማራን ህዝብ ቋንቋ ተማራ ማለት ተግባራዊነቱ ላይ ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም?

13.በሁለቱ ህዝቦች መካከል የጥላቻ ሀውልት ተገንብቶ መሀል ላይ ቁሞብን እያለ ስለ ቋንቋ ከማውራት በፊት የጥላቻ ሀውልት ስለማፍረስ መሰባሰብ አይሻልምን?

እኔ እነዚህንና መሰለ ጥያቄዎችን አንስቻለው።የሆነው ሆኖ ስለቋንቋ እድገት ይወራ ከተባለ ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው።አማርኛ ቋንቋ ብዙ ተመልካች ስላለው ኦሮምኛን በአማርኛ ልክ እናድርገው የሚል የቂል ፉክክር ካልሆነ በስተቀር በዚህ ሰዓት ስለቋንቋ ትምህርት የምንጮህበት አይደለም።ቋንቋን ማወቅ ባይጎዳም ቋንቋ መማር ያለበን፣ ቋንቋውም ማደግ ያለበት ግን ስርዓትን ተከትሎ እንጅ ለእጅ መንሻ መሆን የለበትም።በዚህ አጋጣሚ በአማራ “ክልል” ውስጥ የሚኖሩ ኦሮሞዎችን ባህል፣ ወግ፣ ቋንቌ ወዘተ በማክበርና በማስከበር የአማራ ክልል ሊመሰገን ይገባል።አርዓያ ክልል ነው።ኦሮሚያ ክልል ደግሞ አማራዎችን ከቋንቋ እስከ ባህል፣ ከወግ እስከ አኗኗር ነፃነትን በመግፈፍ ተቀዳሚ ነው።እናም እነ ፕሮፌሰር ሆይ ቋንቋውን ርሱትና ይህንን ሰብአዊነትን ፈልጉት።

ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል ነውና ነገሩ ይህንን የዋህነቱን አይታችው “ስለሚገደሉ ዜጎችህ አንጠይቅልህም፤ዝም ብለህ ቋንቋችን አስተምርልን” አይነት ብልጣብልጥነት የትም አያደርስምና ከዚህ ድርጊታችሁ ትታቀቡ ዘንድ እንጠይቃለን።

Share this post

One thought on “ይድረስ፡- የአማራ ሕዝብ የኦሮሞኛ ቋንቋ ይማራ እያላችሁ ደብዳቤ ለምትጽፉ ሁሉ – ከቋንቋው በፊት ስለሰው ልጅ ነጻነት እንጩህ!!

  1. You article is empty bravado. There is no connection between learning Orlmigna and the rest of issues you try to talk. What a digraceful and reactionary person you are!!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.