ይድረስ ለሀጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰቦች (ሰመረ አለሙ)

አስቀድሜ በተወዳጁ ልጃችሁ ሞት  አንድም ሰብአዊ ፍጥረት በመሆኑ ሁለትም ዜጋ በመሆኑ  ከልባችን  አዝነናል። እንደምታዉቁት በዚህ ወጣት ግድያ ኢትዮጵያዉያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ  ሀዘናቸዉን ገልጸዋል።  የሱን የፖለቲካ መስመር ባይከተሉ እንኳ  በኪነ ጥበብ ቤተሰብነታቸዉ፤ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲሁም ወደፊት ተለዉጦ ኢትዮጵያዊነትን ሊያጠናክር ይችል ይሆናል ከሚል እሳቤ ዜጎች በአሟሟቱ በእጅጉ አዝነዋል። ስለሀጫሉ ሞት ከአንድነት ሀይሉ በኩል ከፖለቲካ እሳቤ ዉጭ በሰፊዉ የሚዲያ ሺፋን ተሰጥቶበታል። በዚሁ አሜሪካ የሻማ መብራት ስነ ሰርአት ሀጫሉን ያስታወሱት የኦሮሞ ብሄረተኞች ወይም ፖለቲካን መተዳደሪያቸዉ ባደረጉ ስብስቦች ሳይሆን ሀጫሉን በወገን መስፈርትና በኪነ ጥበብ ቤተሰብነቱ  ብቻ የመዘኑ ኢትዮጵያዉያን  መሆናቸዉን መግለጽ እንወዳለን። ለጊዜዉ ስለ ሐጫሉ ግድያ የጠራ ነገር አልሰማንም። ሀጫሉ ከእጃችን እያመለጠ ነዉ ተጽእኖ ፈጣሪ በመሆኑ ሳያመልጠን

Source: Link to the Post

Leave a Reply