ደህና ሁን ጨለማ – በላቸው ገላሁን

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107593

ደህና ሁን ጨለማ – ደህና ሁን ጥልመት ከዐባይ ውሃ ማማ – መጣብህ መብራት ከሰል ክረም ደህና – ጭራሮ እንጨት ችቦ ሊተካህ ነውና – የኤሌክትሪክ ሽቦ፤ ኩራዝ ሰንብች ደህና ¬– ሻማና ፋኖስ ፈንጥዢ ኩሽና – በኖ ይጥፋ ጭስ ግብስብሱ ቅጠል – የኩበት ጥፍጥፍ አይብላህ ነበልባል – ይብቃ የእሳት ግርፍ፤ አገሬም ተግ በይ – መንደሬም ድመቂ አሻቅቢ ወደ ላይ – ከሽልብታሽ ንቂ ተማሪ ነጋዴው – ተደሰት ገበሬ ሲገፈፍ ጨለማው – ጠሐይ ሲሆን ዛሬ ዘምሩ አእዋፍ ¬– አራዊት ጨፍሩ የጥልመት ጊዜ ሲያልፍ – ብሩህ ነው አገሩ። ያኔ ታዲያ . . . ያ ሃሳበ ስንኩል – ያ የጨለመበት ትቶ ወደ ፊትን – የሚጓዝ የዃሊት

The post ደህና ሁን ጨለማ – በላቸው ገላሁን appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.