ደቡብ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/144737

ደቡብ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይረዳው ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ፥ ክልሉ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የይቅረታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የባህሪ ለውጥ ያመጡ፣ በእድሜ የገፉ፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ህፃናት ለያዙ እናቶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም መካክል 99 ሴቶች እና 31 የእስር ጊዜ ቅነሳ የተደረገላቸው ታረሚዎች እንደሚገኙበት አንስተዋል።
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ከህብረተሱ ሲቀላቀሉም ለህብረተሰቡ አስተማሪ የሆነ ባሕሪ ሊኖራቸው እንደሚገባም አሳስበዋል።
ህብረተሰቡም ታራሚዎቹ ተቀብሎ ይቀር ሊላቸው እንደሚገባም ነው ምክትል ርእሰ መስተዳደሩ መልዕክታቸውን ያስላለፉት።

Share this post

One thought on “ደቡብ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ2 ሺህ 366 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.