ዲ ኤስ ቲቪ የሻምፒዮኒስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቀጥታ ማስተላለፍ ሊጀምር ነው።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/177608

አማርኛ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ቋንቋ ሆኖ ተመርጧል
ዲ ኤስ ቲቪ የዓለም አትሌቲክ ሻምፒዮና፣ የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም የሻምፒዮኒስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቀጥታ ማስተላለፍ ሊጀምር ነው።
ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የአፍሪቃ ትልቁን የስፖርት ሚድያ ተቋም ሱፐር ስፖርትን ተቀላቀሉ!
በደቡብ አፍሪካ መቀመጫውን ያደረገው እና የአለም አቀፍ ስፖርታዊ ክንውኖች ለአፍሪካዊያን ተመልካቾች በማስተላለፍ የሚታወቀው ሱፐር ስፖርት የሚድያ ተቋም ለኢትዮጵያ ተመልካቾች በአማርኛ ቋንቋ የተመረጡ ውድድሮችን ለማስተላለፍ ለያዘው እቅድ ይረዳ ዘንድ አራት ስመጥር የስፖርት ጋዜጠኞችን ወደ ኮሜንታተር ፖናሉ በይፋ ቀላቅሏል።
በዚህ መሰረት ሃይለ-እግዚአብሔር አድሃኖም፣ ማርቆስ ኤልያስ ፣ ግርማቸው እንየው እና ዮናስ አዘዘ በዛሬው እለት ወደ ደቡብ አፍሪቃ አምርተዋል።
በፋና ሬዲዮ እጅግ ተወዳጁ የስፖርት ዞን አዘጋጆቹ ሰዒድ ኪያር እና መኳንንት በርሄን ጨምሮ የልዩ ስፖርቱ ሀይለ እግዚአብሔር አድሀኖም የብስራት የ4:3:3 ጋዜጠኞች ማርቆስ ኤልያስ እና ዮናስ አዘዘ እንዲሁም የክላሲክ ስፖርቱ ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው አዲስ በተቋቋመው የሱፐር ስፖርት የአማርኛ ፕሮግራም ኮሜታተር እና ተንታኝ በመሆን ዛሬ ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርተዋል፡
 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.