ዶ/ር በያን አሶባ፤ አማራጭ የሚሏቸውን የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ

Source: http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%B6%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%B6%E1%89%A3%E1%8D%A4-%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB%E1%8C%AD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%8F%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%88%98/
https://audiomedia-sbs.akamaized.net/amharic_016cf780-eaf5-4dc2-8869-4b6246ec0e94.mp3

ዶ/ር በያን አሶባ፤ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የድርጅት መምሪያ ኃላፊና ቃል አቀባይ፤ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ያላቸውን ሥጋትና ተስፋ ያንጸባርቃሉ። እንዲሁም፤ አማራጭ የሚሏቸውን የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ። SBS Australia…

Share this post

One thought on “ዶ/ር በያን አሶባ፤ አማራጭ የሚሏቸውን የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ

 1. …በአንድ እራስ አሥር ምላስ”..ትናንት የቷ ኢትዮጵያ? የምን ኢትዮጵያ የሚለው ሰው ዛሬ ደርሶ የአማራና ኦሮሞ አንድነት የኦህዴድ አድናቂ ሆነ!? ልክ አባዱላ ወጥቻለሁ ብሎ ውስጥ እንደቆመው ማለት ነው። ነን ሶቤ? አባዱላ ህወሓት ሥልጣን እንዲቀጥል ኦህዴድ የያዘውን እየበላ እንዲያለቅስ፡ የኦነግን ራዕይ እንዲያስፈፅም፡ ፅንፈኛው የኦሮሞ ዲያስፐር ዝም እንዲል ምን ይደረገለት? ተብሎ ጄ/ር አባዱላ ገመዳ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክን ሊቀ መናብርትንና ጋሻ ጃግሬዎች፡የሜንጫ አብዮተኞችን ጄነራሎች እና የዲያስፐር ዶከተርና ፕርፌሰር ጠብቆች ቃል ይዞ ለህወሓት ከተፍ አለ።(፩) አዲስ አበባ እንዳይስፋፋ (፪) አዲስ አበባ ፊንፊነ የመጫና ቱለማ ጎሳ ኢንዲጂነስ ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን
  መንገድና መንደር በአፋን ኦሮሞ ክርስትና እንዲነሳ (፫) የጁነዲን ሰዶ ህልም አማራን ልጅ፡ ከሲቪል ሰርቪስ ማግለልና መቀነስ እንዲተገበር የራስን ቋንቋ መጫን (፬) ቤት፡ አዳራሽ፡ እስታዲየም፡ ሁሉ ቅድሚያ ለኦህዲድ ካድሬ እንዲሆን (፭) የኦህዴድ ካድሬ አነስተኛ ግብር እንዲከፈል ሱማሌው ደቡቤው አማራውና ሁለተኛ ዜጋ ሲሆን ኦሮሞን ከነጻ አውጭውና መሬትና ሥልጣን ከሰጠው ህወሓት እኩል(ልዩ) እንዲሆን (፮) ኦሮሞ አለኝ በሚለው ፰ ፓርቲ ሲያስቸግር ተለያይተው፡ ሲመች አንድ ሆነው ከውጭም ከውስጥም ሊቀውጡት ተስማሙ። ድንገት ጄ/ል አባዱላ በቃኝ ስትል በአዲስ አበባ መስፋፋት በአንተ አነሳሽነት ተቃውሞ ወተው የኦሮሞ ልጅ ሞቷልና ትጠየቃለህ ሲሉት አሁን አሸማጋይ ሆነ። አደለም እንዴ?

  *** እውነተኛ ኦሮሞ ግን አያት ቅድመ አያቶቻችን የሞቱት ለመላ ሀገሪቱ ትግራይንም ነጻ ለማወጣት እንጂ ከህወሓት ለፍንፊነ እና ለሽሮ ሜዳ ሰንዳፋን አሌልቱ ድንጋይና ውሃ አደለም…ያነሰም የብዛም ሳይሆን ጎነደርም፡ ጎጃምም፡ ሸዋም አፋርም፡ አሰብም፡ ጣናና አባይ ወንዝ ከነግድቡ ኬኛ! ሲሉ ጉድ ፈላ። ተጨቆንን ተረገጥን ማንነታችንን ህወሓት በ፲፩፱፹፫ በሕገመንግስት(የጫካ ማኒፌስቶ ሰጠን ብለው የሚሞላፈጡ ጡረተኛ የዲያስፐር ቦልጥቀኞች፡ ሌንጮ ለታ፡ ሌንጮ ባቲ፡በያን አሶባ፡ዳውድ ውርጭሎቹም ፕሮፌሶሬ እስቅኤል ጋቢሳ፡ ጸጋዬ አርአንሳ፡የፖለቲካ ተንታኝና በታኝ ጀዋሪው መሐመድ ተዋረዱ…ዙሪያውን ይቀሳፍታሉ። መጤና የምንይልክ ሰፋሪ ያሉትም ፮፻ሺህ የዋህ ኦሮሞን በከብት መኪና ጭኖ አበረረላቸው! “በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” ነን ሶቤ?
  *** ወያኔ የሽግግሩ አካል ይሁን ሲሉ..ለደም መፋሰስ ለሀገር መፍረስ፡እንዳይኖር የሚሉ ቱማታ መልሱ ትፍረስ ትበታተን በፍርስራሹ ላይ ኦሮሚያን እንመሠርታለን ያላችሁት እናንተ አደላችሁምን!? የውሸት ታሪክ መፈልሰፍ፡ የቅርስ ማጥፋት፡ የትውልድ ማምከንና ማባከን በእርግጥ እንደ ኦነግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ውርደት፡ አሁን የኦሮሞ አዲስ ትውልድ ላለበት የዜግነት መላሸቅ፡ ላለበት የዕውቀተና የኢኮኖሚ የበይ ተመልካችነት፡ የማንነት ችግር (ቀውስ) የዳረገው የኦሮሞ ኤሊት(ኤሊ) አደለምን? ህወሓትን አማራና ኦርቶዶክስ እንዲያጠፋ፡ የተራዳው ደግፎ ያቆየው ማን ሆነና? አሁንም ህወሓት/ኢህአዴግ ይቀጥል ሲባል ለሽግግሩ እጅ መንሻ፡ የሰጣችሁን ልዩ ካርታና ጥቅማጥቅም እንዳያከትም አደለምን!? ለመሆኑ ኦሮሞ ላለፉት ፳፯ ዓመት ካልተጠቀመ አጥፊው ህወሓት የልማት አውራ፡ መሪ ተዋናይ ይሁን (ነው) ማለት ምንድነው? ነባሩ ችግራችሁና ቁርሾው የዓላማ ሳይሆን የሥልጣን መሆኑ አደለምን!?
  *** የታሰሩ ሁሉ ያለቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!?
  _፟ የዚህ ቡድን ምኞትና ተስፋ ቅደም ተከተሉ ተምታቷል፡መጀመሪያ ዕውቅና ሳያገኙ ለትግል ከኤርፖርት መባረራቸው በራሱ ትምህርት አልሰጣቸውም። “አሁን ሰላም የለም፡ ግዜው ለእናንተም ለእኛም ጥሩ አደለም፡ ባይሆን ለሚቀጥለው ምርጫ ትመጣላችሁና ቶሎ ውጡ” ቀጭን የስልክ ትዕዛዝ ሆቴላቸው ድረስ። ቀድሞም ለህወሓት ለዋሉት ውለታ ኤርፖርት ድረስ በአጃቢ ተሸኝተው፡ኦሮሞን በተመለከተ ሓሳብ ሲያስፈለግ፡ ለገሰ መለሰ አውሮፓና አሜሪካ ሌሊት እየደወለ ይመክራቸውም ያፅናናቸው አልነበረምን?
  የሕግ ምሁሩ እሥረኛ ይሰናበት ይላል?…ለመሆኑ በምን ላይ ተስማምታችሁና ተማምናችሁ ነው? መንግስት ጥፋተኛ ባሰረ ቁጥር በአድማ እናጠፋሃለን ከተባለ እሥረኛ በነጻ ከተፈታ ይህ ሀገር ሳይሆን የሽፍታ ቡደን ነው ማለት ነው።
  * ሁሉም የፖለቲካ ቦድኖች ይሳተፉ?
  __፟ መጀመሪያ ያለውን ተለጣፊ፡ ደጋፊና/ተደጋፊ.. ተቃዋሚ/ተቋቋሚ ቢያንስ ወደአራት የፖለቲካ ፓርቲ መቀነስን በአዋጅ መስማማት፡ ፻ ሚሊየን ፻ የፖለቲካ ፓርቲ ዕድር ነው ዕቁብ!? የሰንበቴ ማኅበር? ጥራት ብቃት!!! አዲስ የፖለቲካ ማኒፌስቶ ለሕዝብ በግልጽ እንዲደርስ ሚዲያውንና በነጻነት በሀገሪቱ ክፍለሀገራት ሁሉ ተዘዋወሮ ማስተዋወቅ፡ አባላት ማሰባሰብን ማመቻቸትና በቂ ዕርዳታና ትብብር ማድረግ፡ ሁሉም ተሳታፊ ደጋፊና ተቀናቃኝ ዓላማውን አውቆ ሕዝቡ በቋንቋ በነገድ ሳይሆን በዕውቀት ላይ በተመሠረተ ፓርቲ(መርህ) በምርጫው/በፍላጎቱ /ባመነበት እንዲሳተፍ፡እንዲመርጥና እንዲመረጥ ነዋሪው እንዲከተለውና ሠርቶ እንዲያሰራ ማድረግ፡፡ ከዚህ የወጣ/ያፈነገጠ ቡድን፡ አሸባሪ፡ ፅንፈኛ፡ ዘረኛና ጎጠኛ ተብሎ እንዲቀጣ ከአሸባሪው ሕግ የወጣ(የተለየ) ከወንጀለኛው መቅጫ ሕግ የሚጠነክር አዋጅ በምክር ማፅደቅ። አንቀጽ ፴፱ በሀገሪቱ ግንጠላና ብተናን በሚከለክል አውጋዥ /አስገዳጅ ዓረፍተ ነገር መቀየር። አማራጭ የሌለው አሠራርና የሕግ ተጠቃሚና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው።።

  *የአማራና ኦሮሞ አንድነት፡ የፖለቲካ መሪዎች(ልሂቃን) ብልጠት ሳይሆን፡ የወጣቱ ንቃተ ኅሊና መዳበር፡ የውሸት ታሪክና የአማራ ጥላቻ ፖለቲካ አጉዳይ! አክሳሪ! አሳፋሪና አባይ! ስለሆነ፡ አንድነት ኅይል፡ ኅብረት ብርታት፡ ጉልበት ነው ብለው ስላመኑ ነው። ከዚያም እናንት ሆዳድአደር ፡ አድርባይ፡ አውርቶ አደር፡ ዲያስፐርስ(እናንተ ውጭ ያላችሁ የጠፋት ቫይረሶች) ባላችሁበት ቅሩ፡ ያጥፋችሁ! እኛው በእኛው ተባብረን ስሕተታችንን አርመን ሁሉ ኬኛ እናሸንፋለን አሉ እሰየው!!! ይሆናልም! በያን አሶባ ሌላውን በኢ-ዲሞክራሲነት ሲወቅስ እራሱን ዲሞክራት ማድረጉ በራሱ ምክሩ አልገባውም!?
  **ሕወሓት ኖረም አልኖረም፡ የውስጥ ዓረምና እሾክ እስካለ ድረስ መቆርቆርና መጎርበጡ ይቀጥላል! እያንዳንድህና ሁልህም አላለቅስም በል! እንጂ ለቅሶዬ አልደመቀም ብለህ አትቆጭ! እሥረኛ ቁስለኛ እሬሳ ከምትቆጠርና በቁጥር ቀመር አዘጋገብ ከምትጣላ ! እንቢኝ በነጻነቴ ኢትዮጵያ ናት እናቴ በል። ድል ለተገፋው ሕዝባችን ይሁን!!።

  Reply

Post Comment