“ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም” ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/190535

ዶ/ር አብራሃም በላይ Awramba Times ላይ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ኢንሳን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ መሆናቸውን በመጠቆም ወደ ኢንሳ የገቡት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ባስመዘገበው ውጤት እና መልካም ስነ-ምግባራቸው መሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር አብራሃም ለውጡን ተከትሎ የኢንሳ መስራች አመራሮች (ጓደኞቻቸው) በተለያየ የስልጣን ቦታ እና የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ገብተው መለያየታቸው እና ሁሉም እንደበፊቱ ለአገራዊ ዓላማ በአንድነት መስራት አለመቻላቸው እንደሚያሳዝናቸው በመጠቆም ከጓደኞቻቸው አንድም ሰው እንዲታሰር እና የሌላ አጀንዳ አራጋቢ ሆኖ ማየት እንደማይፈልጉ ለአገር ልማት ብቻ መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ዶ/ር አብረሃም በላይ ለትግራይ ጥቅም እንታገላለን በሚል ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ እና ተከታዮቹን ሃሳብ እንደሚቃወሙት በዚህም መሰረት ለአገር መስራቱን እንደቀጠለ በመግለፅ የጄ/ል ተክለብርሃንን ሃሳብ አሁንም እንደማይቀበሉት እነሱ ግን በስጋት ወደ መቀሌ መሸሻቸውን ጠቁሞ ማንም ሰው ወንጀለኛ ከሆነ ደግሞ ትግራይ ስለሄደ ከመታሰር አይቀርለትም! የትግራይ ህዝብ ለውጥ ፈላጊ እንጂ የለውጥ አደናቃፊ አይደልም የትግራይ ህዝብ አሁን ፌዴራል መንግስት ጫና እየፈጠረብን ነው ተብሎ ስጋት ውስጥ እንዲኖር ሆን ተብሎ የተለጠጠ ወሬ እየተነዛበት ነው እንጂ ምንም ስጋት የለም ብለዋል የትግራይ ህዝብም የለውጡ አካል ሆኖ ሳለ የመጣውን ለውጥ የእኔ አይደለም ብሎ መሸሸ ልክ አይደለም።
ዶ/ር አብይ አህመድ እኛ ትግሬዎች ለትግራይ ህዝብ ያላደረግነውን ሲያደርግ የነበረ አሁንም ኣብዛኞቹ ጓደኞቹ የትግራይ ልጆች ናቸው መጀመሪያ አከባቢ የንግግር ግድፈቶች ነበሩ እሱን ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ስለ ሌባ ሲናገር የትግራይ ህዝብን ሌባ ብሎ ሰድቧል በሚል እየለጠጡት ስለሆነ እንጂ ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.