ዶ/ር ወርቅነህ ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ቢን ሳድ አል ሞራኪሂ ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8B%88%E1%88%AD%E1%89%85%E1%8A%90%E1%88%85-%E1%8A%A8%E1%8A%B3%E1%89%B3%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8B%8D%E1%8C%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%9A%E1%8A%92/

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ቢን ሳድ አል ሞራኪሂ ጋር ተወያዩ ።

ሚኒስትሮቹ  የሁለትዮሽና ሁሉን አቀፍ ግንኙነቶቻቸውን  ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው መወያየታቸው ነው የተነገረው፡፡

የሀገራቱ  ግንኙነት የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ መሆኑን ነው ዶክተር ወርቅነህ የገለፁት፡፡

ይህንን ግንኙነታቸውም በአሁኑ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና በህዝብ ለህዝብ ትስስር ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ቢን ሳድ አል ሞራኪሂ በበኩላቸው ፥በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴም ሀገራቸው እንደምትደግፍ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም  ሚኒስትሮቹ ሁለቱ ሀገራት የስራ ስምሪት ስምምነት ለመፈራረም በሚችልቡበት ሁኔታ ላይም መምከራቸው ነው የተገለፀው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተዘጋጀው ሰነድ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ታይቶ በቅርቡ እንዲፈረም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚሰሩ ዜጎቿ መብት እንዲከበር በቅርቡ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከተበባሩት አረብ ኤሚሪቶች ጋር የስራ ስምሪት ስምምነት መፈራረሟ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.