ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንዴትና ለምን ተመረጡ???

Source: http://www.mereja.com/amharic/566084

ወያኔ/ኢሕአዴግ ትወናውን እንዴት ችለውበታል ባካቹህ! ሕዝቡን እኮ በጥፍሩ አቁመውት ሰነበቱ! ማን የቀረ አለ? በተለይ ደግሞ እነማን ገረሙኝ መሰላቹህ አቶ ኃይለማርያም መልቀቂያ የጠየቁት በገዛ ፈቃዳቸው ሳይሆን እንዲጠይቁ ተደርገው እንደሆነ የሚያውቁ ወይም[…]

Share this post

One thought on “ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንዴትና ለምን ተመረጡ???

 1. ኅይለመልስ ደስአለኝ “ሀገሪቱን ላለፉት ፮ ዓመት ችግር ላይ ስለጣልኳት ሥራዬ መቀጠል አልችልም። ልቀቁኝ ግን ተጠቅላይ ሚ/ር ሆኜ ‘የመፍትሔው አካል መሆን እፈልጋለሁ” እንዴት ነው ነገሩ? መጀመሪያውኑ ችግሩን ለምን ፈጠረው? አሁን ሁለተኛ ም/ጠ ሚኒስተር ሊሆን ነው? ወይስ የአብይ መሐመድ የመለስ ራዕይ አስተማሪና
  በጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የህወሓት ጉዳይ ፈጻሚ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፡ የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ጠቅላይ፡ ምርጫ አቶ ደመቀ ራሱን እንዲያገል ተደርጎ ዶ/ር ዐቢይ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጡ ለፉክክር በቀረቡበት ምርጫ ተገኘ የተባለውን ብአዴን ፵፭ ቱም ድምፅ፣ ኦሕዴድ ፵፭ቱም ድምፅ፣ ደኢሕዴን ፲፰ ድምፅ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፡፡ ሕወሓት ፴፪ ድምፅ፣ ደኢሕዴን ፳፯ ድምፅ ለአቶ ሽፈራው፡፡ ሕወሓት ፪ ድምፅ ለደብረጽዮን፡
  ድምፅ -ተዐቅቦ ፰ ድምፅ፡ በምርጫ ያልተገኙ ፫ ተባለ።

  ዶ/ር ደብረፂዮን እንደተናገሩት ትግራይን ለማስተዳደር ከተመረጥኩ አጭር ጊዜ ስለሆነኝ መመረጥ አልፈለኩም ነበር “አትምረጡኝ ብዬ ቅስቀሳ አድርጌያለሁ” ዶ/ር ደብረፂዮን «መመረጥ ካልፈለጉ ለምን አንደ አቶ ደመቀ ራስዎን አላገለሉም»
  “የሕወሓት የበላይነት እንደሌለ ግልጽና ፉክክር የነበረበት ለየት ያለ ምርጫ መሆኑን ለሕዝብ ለማሳመን ሲባል”
  ህዉሃት በ1983/84 ዓም ኦነግን ይዛ ቀሪዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አግልላ ምናምንቴ ህገ መንግስት እና ኢትዮጵያዉያንን የሚያባላ ክልል ያጸደቀች ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያዉያንን እና አለም አቀፍ ማህበረሰብን ማታለል ችላ ነበር። በድጋሚም በ1997 ዓም ምርጫ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ለዉጥ ፈልጎ ቅንጅትን ሲመርጥ ሶስት ጣምራ ስትራቴጂዎችን ተጠቅማ ህዝባዊዉን ሀይል ከጫዋታ ዉጭ እንዲሆን አድርጋዉ ነበር። ይሄዉም የቀኝ ክንፍ አክራሪ ሀይሎች መጡብህ የሚል ማስደንበሪያ፣ የጉልበት ስልት እና ቅንጅቱን እራሱን ገብቶ የመከፋፈል ስትራቴጂዎችን በማጣመር ቅንጅቱን ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ችላ ነበር። የአዲሱ ሴራ ሲተነተን… ሸንቁጥ
  (ሀ) ኦህዴድ እና ብአዴን ከህዉሃት ጋር ትግል ዉስጥ ገብተዋል የሚል ትርክት ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደረገ።የኦሮሞ ብሄረተኞችን እነ ጀዋርን ሳይቀር ወደ ኦህዴድ ደጋፊነት እንዲያዘነብሉ ማድረግ የሚያስችል የድርሰት ሴራዉ እንዲጦፍ ተደረገ::
  (ለ)አባይ ጸሃዬ እና አቢይ ተቧቀሱ፣ ደመቀ እና ደብረጺዮን ተደባደቡ፣ ቲም ለማ እና ገዱ ግንባር ፈጠሩ በሚል ትርክት በለዉጥ ጥማት የሚንገበገበዉን ኢትዮጵያዊ ብዙሃን ትኩረት ወደ ህዉሃት ድራማ ትርክት እንዲሳብ አደረጉት።
  (ሐ) አቦይ ስብሃት ብአዴኖችን ሰብስቦ ለምን ከኦህዴዶች ጋር መከራችሁ ብሎ አስጠነቀቃቸዉ የሚል ትርክት ከባህርዳር የብአዴን ካድሬዎች እንዲሰራጭ ተደረገ። ድራማዉን በደንብ ለማጦፍም ኢትዮጵያዊነት ሲሰበክ ለመስማት የሚቋምጠዉን ሰዉ የሚያማልል “ኢትዮጵያዊነት ሱሴ” የሚል ትርክት በስፋት እንዲሰማ ተደረገ።
  (መ) በሚገርም እና ለማመን በሚያስቸግር ፍጥነት ኢትዮጵያ የሚል ቃል ሲጠራ ጆሮዉን ያሳክከዉ የነበረዉ ጀዋር ሳይቀር ኢትዮጵያዊነት ሱሴ የሚለዉ ትርክት ደጋፊ እንዲሆን የቲም ለማ ሀይል እያሸነፈ ነዉ፣ የህዉሃት ጉልበቱ እየተንቀጠቀጠ ነዉ የሚል አንደምታዎች መሰራጨት ጀመሩ::
  (ሠ) ለማ መገርሳ እና አቢይ ቦታ እንዲቀያየሩ እና አቢይ የኦህዴድ ሊቀመንበር እንዲሆን ሲደረግ ወያኔ ከኋላ ሆና ድራማዉን ብትቆምርም ይሄ የአቢይ እና የለማ ቦታ ልዉዉጥ የጀግንነት እና የብልሃት ትርክት እንዲላበስ ወደ ተቃዋሚ ጎራዉ እንዲስፋፋ ተደረገ።ኢሳት የኦህዴድ ድምጽ እንዲሆን እና እነ አቢይን እንዲያጀግን አስተማማኝ ስራ ተሰራ::ኢሳት ኢህአዴግን የከፋፈለ መስሎት በዋናነት የወያኔን ድራማ ማስፈጸሚያ ሚዲያ ሆኖ ቁጭ አለ።
  (ረ) በጠቅላይ ሚኒስቴር ሹመቱ ላይ ህዉሃት በአቢይ ደስተኛ እንዳልሆነ ለማስመሰል ደመቀ መኮንንም ለማጀገን እንዲሁም የብአዴንን ክብር ጠብቀዉ ከኦህዴድ ጋር የጠበቀ ፍቅር ናቸዉ፡ ለማስባል ብሎም በብዙሃኑ የአማራ እና የኦሮሞ ተወካዮች የተመረጠ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነዉ ለማስባል አቢይ በዋናነት በኦህዴድ እና በብአዴን ድጋፍ እንዳለፈ እንዲመስል ድራማዉ አግባባዊ ትረካዉን አስቀምጧል።
  **በየአካባቢዉ የተነሱ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አንዱም እንኳን አልተፈታም። ሆኖም ወያኔዎች እና አስመሳይ ተቃዋሚዎች የተቃዉሞዉን አቅጣጫ እኛ የመረጥንልህን ጠቅላይ ሚኒስቴር ትግሬ ሳይሆን ከዚህ ብሄር በመሆኑ ተነስተህ አጨብጭብ የሚል አንደምታ እየሰበኩ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የአማራ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የትግሬ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚል አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በዋንኛነት የዲሞክራሲ አስተሳሰብ እና መርህ እዉን የሚሆበት ስርዓት እና በህግ የበላይነት የሚመራ ተቋማት እዉን ሆኖ ማዬት ነዉ። ይሄን ደግሞ ገማሁ፣ በሰበስኩ፣ በወንጀል ተጨማለቅሁ፣ በሙስና ከረፋሁ ብሎ እራሱን ደጋግሞ በህዝብ ፊት ባዋረደዉ ኢህአዴግ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም። እንቶኔም ሄደ እንቶኔም ተተካ ሁሉም የገማዉ ስርዓት አካል እና አባል ነዉና። “ሲል ሸንቁጧል።
  *በጣም አስገራሚና አስደንጋጩ ነገር ሁሉምና እያንዳንዱ ቦልጥቀኛ ዲያስፐር ተቃዋሚና ተቋቋሚ ሁሉ ለዓብይ መሐመድ አሊ ነገዱን ትምህርቱን፡ማዕረጉን፡ የሥራ ደርሻውን፡ዕድሜውን፡ ቤተሰቡን ጓደኛና ጎረቤቱን እያጣቀሰ መረጃና ማስረጃ አድርጎ የመጀመሪያውን የሕዝብ ንግግር፡የመጀመሪያውን ፻ ቀን የሥራ ዕቅድ፡የመጀመሪያውን ስድስት ወር መርሃ ግብር ነድፈው ለጥፈዋል፡ ይቺ ናት ሀገር! ይህ ሀገር በወሮ በላ መወረሩ ሳያንስ ከዕድርና ዕቁብ ያነሰበት ሕዝብ የተናቀበት ግርም ይላል። ዶ/ር ዓብይ መሐመድ አሊ ሆይ፡ ይቺ ማንቆለጳጰስ ለመለስም አልበጀች ይልቁንም እንደአጀማመርህ ኢትዮጵያዊነትን ስበክ! የክልል የከብት ጋጣ ጎን ድልድይ ሥራ! ብሔርን ከወረቀት መታወቂያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም አስለውጥ! ለህወሓት ሐሳብን አምኖ፡ ነገርን ማሳመንን፡ በሕዝብ መታመንን አስተምር! አሳታፊ እንጂ አግላይ አትሁን! የታሰረ ሕዝብ፡ቋንቋ፡ሰንደቅና ሀገርን አስምር! በመረጠው የሚኖር፡በፈለገውና ባመነው የሚያስብ ትውልድ እንዲኖር አበረታታ! አፍራሽ ሳይሆን ገንቢ ትውልድ እንዲኖር የወጣት ሥነልቦና ቀረጻ ቅድሚያ ሥጥ! ተምሮ አስተማሪ እንጂ ሳይማር የሚያደነቁርና የሚያባላ ካድሬ፡ ሠርቶ ጥሮ ግሮ እንዲበላ አሰናብት!ሕዝብ የነበረ ያለ የሚኖር እንጂ “ማንነታችሁን የማታወቁ የማትታወቁ በ፩፱፹፫ በእኛ የተፈጠራችሁ፡ ለእኛ የምትኖሩ፡ያለ እኛ የምትበታተኑና የምትጠፉ ብርቅዬ ተናጋሪ እንስሶች” የሚለውን የጫካ ማኒፌስቶ የከተማ ሕገ ጠርንፍ በባለሙያ አስጠና ! አስተምር አንቃ አደራጅ…ከጉልበት(ከመሳሪያ) ወደዕውቀት(ሥራ) ሽግግር እንዲኖር ይሁን መልካም ዕድል!!!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.