ዶ/ር ደብረፅዮን ሞተዋል ተብሎ ከተሰራጨው የሐሰት ዜና ጋር በተያያዘ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል በሕግ ይጠየቃል ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/180868

ከትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ
ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር፣ የትግራይ ብሄራዊ ክልል መንግስት ም/ርእሰ መሰተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ሂወታቸው አልፈዋል ብሎ በዛሬው እለት ያሰራቸው ነጭ የፈጠራ ወሬ ፈፅሞ ሀሰት መሆኑን ለመላው ህዝባችን ማሳወቅ እንወዳልን፡፡

ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር waltainfo.com በሚል ፌስቡክ ገፁ ላይ ዛሬ ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም ከሰአት በኅላ ያሰራጨው ሀሰተኛ የአሉባልታ ወሬ፣ ይህ የመገናኛ አውታር ባለፉት አመታት በትግራይ ህዝብ ላይ የብሄር ተኮር ጥቃት እንዲደርስ ስያካሂደው የነበረ ዘመቻ ኣካል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡
በመጨረሻም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋልታ ኢንፎረሜሽን ማእከል የተባለ የመገናኛ አውታር በህግ የሚጠቅይ መሆኑን ይገልፃል፡፡
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ
ታህሳስ 03/2012 ዓ/ም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.