ጀስቲፋይድ አኮርድ 2019 የተባለ የ16 ቀናት ወታደራዊ ስልጠና ተጀመረ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131448
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/AB36F91C_2_dwdownload.mp3

DW : የአሜሪካ ጦር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች አገሮች ጋር በመሆን ጀስቲፋይድ አኮርድ 2019 የተባለ የ16 ቀናት ወታደራዊ ስልጠና ለመስጠት ያዘጋጀውን መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ስልጠናው በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ የሚሰጥ ነው።


የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ጦር በትብብር ያዘጋጁት ወታደራዊ ስልጠና ከ13 ሃገራት የተውጣጡ 1100 የሚሆኑ ሲቪሎች እና ወታደሮች ይሳተፉበታል። ሰልጣኞቹ ይህንን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ የሃገራቸውና ምድብ ስፍራቸው ይመለሳሉ።
ስልጠናው በተለይ የአልሸባብ ስጋት ባጠላበት የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማስፈን የሚያስችል ወታደራዊ ክህሎት እና ዝግጁነትን ለማጠናከር ያለመ ነው። አመታዊ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስልጠና ሰላምን በማስፈን ረገድ አለም አቀፍ እና ዘርፈብዙ ልምዶችን ያሻሽላል ተብሏል።
Äthiopien Addias Baba | US Militär in Partnerschaft mit Äthiopische Streitkräften und weiteren Organisationen (DW/S. Mushie)
ወታደራዊ ስልጠናው አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚደረገውን ሽብርን የመዋጋት ተግባር እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ስልጠናው በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮን (አሚሶም ) ስራን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
አሜሪካ ከዚህ በፊት በቁሳቁስ ታደርግ የነበረውን ወታደራዊ ድጋፍ አሁን በእንዲህ ያለ መልኩ ማድረጓ በተለይ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስር ለሰላም ማስከበር የምታደርገውን ተሳትፎ ግምት ውስጥ ማስገባቷን አመልካች መሆኑ በመክፈቻው ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.