ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎቼ ተጠርተዋል ፤ መኖሪያዬ በታጣቂ ኃይሎች ተከቧል አለ ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/160308

ጠባቂዎች ከሰአታት በፊት የጅዋርን ጊቢ ለቃቹ ውጡ ተብለዋል። ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው! ራሱ ፌስቡክ ላይ ፅፏል። የስልክ ንግግሮችንም ይፋ አድርጓል።
እንዲህም ሲል ፅፏል ፦ ( ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ – በብዛት ወደ መኖሪያዬ እየተሰማራ ያለው የታጠቀ ሀይል ወደኋላ እንዲመለስ በአጽኖት እንጠያቀለን። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደግቢ የሚንቀሳቀስ ግለስብም ሆነ ቡድን ላይ ጥበቃው የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ለሚከሰትው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስደው ያላንዳች ምክናያት እና ማሳሰቢያ ሀይል ያሰማራው አካል መሆኑን ህዝቡ እንዲያውቅልን እንፈልህጋለን። Jawar Mohammed )

ጃዋር የሚታሰር ከሆነ የእሱን ደጋፊዎች ከሚያስቆጣ ማንኛውም አይነት ፅሁፍና ንግግር እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እወዳለሁ። አላስፈላጊ የቃላት ጦርነት በመግጠም ግጭትና ሁከት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ ከማድረግ መቆጠብ አለብን። በተቻለ መጠን ሁኔታውን ለማረጋጋት ብንሞክር የተሻለ ይመስለኛል። #MinilikSalsawi

Share this post

One thought on “ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎቼ ተጠርተዋል ፤ መኖሪያዬ በታጣቂ ኃይሎች ተከቧል አለ ።

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.