ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደሩ መሆኑን ይፋ አደረጉ

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%8C%86-%E1%89%A3%E1%8B%AD%E1%8B%B0%E1%8A%95-%E1%8B%B2%E1%88%9E%E1%8A%AD%E1%88%AB%E1%89%B2%E1%8A%AD-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2%E1%8A%95-%E1%8B%88%E1%8A%AD%E1%88%88%E1%8B%8D-%E1%88%88%E1%8D%95/

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር በሚካሄደው የምርጫ ዘመቻ እየሚሳተፉ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ጆ ባይደን  ጉዳዩን አስመልክተው በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ በአሁኑ ወቅት  በዓለም ደረጃ ያለት መሰረታዊ እሴትና ተቀባይነት  አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል ።

ይህን ችግር ለመፍታትም በሚቀጥለቀው ምርጫ ፕሬዚዳንት ዶናላድ ትረምፕን ለመፎካከር  የምርጫ ዘመቻ ለመሳተፍ መወሰናቸውን አስታውቀዋል ።

በዚህም አወዛጋቢውን ፕሬዚዳንት ዶላንድ ትራምፕ ለመወዳደር ከወሰኑ በርካት ዲሞክራቶች መካከል አንዱ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

በቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኦባማ አስተዳደር ወቅት የሁለት የሥራ ጊዜ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ባይደን በቬርሞንት ክፍለ ግዛት ከሌሎች ተፎካካሪዎች ጋር በዲሞክራሲያዊ ፖርቲ ለመመረጥ ይወዳደራሉ።

የ76 ዓመቱ ባይደን ከዚህ በፊት ባካበቱት ተሞክሮ ማለትም በውጭ ፖሊሲ፣ በወንጀል ፍትህና በሀገር ውስጥ ፖሊሲ ያላቸው ዕውቀት ከፈተኛ ነው ተብሏል።

ባይደን ለምርጫ ዘመቻ የሚሆን ገንዘብ በደንብ ማሰባሰብ ከቻሉም  ያላቸውን የካበተ ልምድ በመጠቀም በምርጫው የሚወዳደሩ ዲሞክራጾችን በብርታ ሊፎካከሩ ይቻላሉ የሚል ግምት አግኝተዋል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.