ጉዳዩ፥ በልዩ ልዩ ምክንያት የተበተነውን የኢትዮጵያ ሰራዊት ለሃገሩ ዘብ እንዲቆም ስለማድረግ!

ክቡር ዶ/ር ዓብይ ሆይ፤ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታየ ከባሕር ማዶ ይድረስዎት። ኢትዮጵያዊያንን ሲአስጨንቅ የነበረውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት እንዲፈፀም በማድረግዎ እንኳን ደስያለን። በግድቡ ግንባታ፤ በዓለማቀፍ ድርድርና ውይይት ለተሳተፉ ሁሉ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው። ከሁሉም በላይ መቀነት ፈተው የረዱ እናቶች፤ ኮረጇቸውን አራቁተው የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ክብረት ይስጥልን። እኔ የያትውልድ አካል ነኝ። ትውልዱ በግራ ዘመም ፖለቲካ ያበደበት። ግራ እጅ ተራማጅ፤ ቀኝ እጅ አድሃሪ ሆኖ አካሉን ከሁለት ጎራ ከፍሎ የተፋጀበት። አንድ የተደራጀ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ድርጅት ሳይኖር ስርነቀል ለውጥ የጠየቀ ትውልድ። ስለሆነም አሁን ላይ ሆኘ ይህን ሃሳብ ሳቀርብ የድሮ ስርዓት ናፋቂ ተብየ እንደምፈረጅ እረዳለሁ። ሃሳቤ ተቀባይነት አግኝቶ ኢትዮጵያ ከዳነች ፍረጃውን በፀጋ የምቀበለው

Source: Link to the Post

Leave a Reply