ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ምክንያቱ ባልታወቀ ኹኔታ በርካታ ጉማሬዎች እየሞቱ እንደሚገኙ ተጠቆመ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/111563

Image result for በርካታ ጉማሬዎች ሞቱ
በደቡብ ክልል ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ምክንያቱ ባልታወቀ ኹኔታ በርካታ ጉማሬዎች እየሞቱ እንደሚገኙ ተጠቆመ። የደቡብ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት እንዳስታወቀው ጉማሬዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እየሞቱ የሚገኙት ፓርኩን አቋርጦ በሚያልፍው የጊቤ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ ነው።
በሳምንቱ የመጀመሪያዎቹ ቀናት 4 ጉማሬዎች ሞተው መገኘታቸው ለፓርኩ ጥቆማ የደረሰ ቢሆንም፤ ከዚያ በኋላ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሞት መጠናቸው በመጨመር አሁን ባለው ሁኔታ 28 መድረሱን ጽ/ቤቱ ዐስታውቋል።
በአኹኑ ወቅት ከደቡብ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት እና ከፌደራል የዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የተውጣጣ የባለሞያዎች ቡድን በስፍራው ደርሶ የምርመራ ሥራ መጀመሩን የደቡብ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ለማ መሰለ ለዶይቸ ቬለ (DW) ገልጸዋል።
«ይኼ የተፈጥሮ ክስተት እና የእንስሳት በሽታ ቢኾን አብዛኛው ባለቀ ነበር። ወጣ ያሉት ካልኾኑ በስተቀር አኹን ውኃ ውስጥ ያሉት እንዳሉ እያየን ስለኾነ ይኼ በተለየ መንገድ ሊኾን ይችላል የሚል ጥራጣሬ አለን።»ጉማሬዎቹ በድንገት የመሞታቸው ምክንያት ተፈጥሯዊ ይኹን ሰው ሠራሽ ለማጣራት የዞኑ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ይጠቁማል።
ዶይቸ ቬለ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.